አዲስ አበባ —
መንግሥት እና አደባባይ የወጡ ሰልፈኞች ለመነጋገር ሰላማዊ መንገድ እንዲፈልጉ እርስ በእርሳቸው እንዲደማመጡም አሳስበዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ ዓለምአቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅት(የዩኤስአይዲ) የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ለስሊ ሪድ ስለ ኢትዮጵያ የተቃውሞ ሰልፎች ያነሱት በአዲስ አበባ በተከበረው እና በርካታ እንግዶች በተገኙበት ዓለምአቀፍ በዓል ላይ ነው። በዚህ ዓለምአቀፍ የሰብዓዊነት ቀን በሚከበርበት በዓል ላይ ንግግር ያደረጉት ሚስ ለስሊ ንግግራቸው የጀመሩት በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑት ፓትሪሻ ሃስላክ መገኘት አለመቻላቸውንና የእሳቸውን ሰላምታ በመግለጽ ነው።
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።