ጉባዔው የተከፈተው በእንደራሴና የፓርቲው ሊቀመንበር በሚስ ዴቢ ዋሰርማን ነው፡፡
ከንግግር አድራጊዎቹ አንዷ የሃገሪቱ ቀዳሚት እመቤት ሚሸል ኦባማ ሲሆኑ ስለአሁኑ ምርጫ ዓላማ፣ ስለባለቤታቸው ባራክ ኦባማ እና ስለሌሎችም የወቅቱ የምርጫ አጀንዳ የሆኑ ጉዳዮች ንግግር አድርገዋል፡፡
የጉባዔው ተሣታፊ በሆኑ የዴሞክራቲክ ፓርቲው ልዑካን ላይ ከፍተኛ ስሜትና ዝግጅት እንደሚታይ ጉባዔውን እየተከታተለ ያለው ዘጋቢያችን ተወልደ ወልደገብርዔል ከሥፍራው ተናግሯል፡፡
ከተሰብሳቢዎቹ መካከልም አንዳንዶቹን አነጋግሮ “ወደፊት መቀጠል እንጂ ወደኋላ መመለስ የለብንም” ብለውታል፡፡ የወቅቱ የባራክ ኦባማ የምርጫ መፈክርም “ወደፊት” የሚል እንደሆነ ይታወቃል፡፡
ልዑካኑ አክለውም “ሃገራችንን መገንባት ካለብን መጀመር ያለብን ብዙኃን ከሆኑት ባለመካከለኛ ገቢ አሜሪካዊያን ነው” ብለዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተወልደ ወልደገብርዔል ያዳምጡ፡፡