በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ረጂፕ ታይፕ ኤርዶዋን ከፕረዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን ጋር ተወያዩ


የቱርክ ፕረዚዳንት ረጂፕ ታይፕ ኤርዶዋንና የሩስያ ፕረዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን
የቱርክ ፕረዚዳንት ረጂፕ ታይፕ ኤርዶዋንና የሩስያ ፕረዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን

የቱርክ ፕረዚዳንት ረጂፕ ታይፕ ኤርዶዋን ቱርክን ከሶርያ ጋር የሚያዋስነውን ድንበር በሚመለከት ወታደራዊ ስትራቴጂ ለማውጣት ሲሉ ከሩስያው ፕረዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን ጋር ዛሬ ተገናኝተው ተነጋግረዋል።

የኩርድ ተዋጊዎች በሠዓታት ውስጥ ከሚያበቃው የተኩስ ማቆም ሥምምነት በፊት ከአካባቢው ካልወጡ በስተቀር በተዋጊዎቹ ላይ የማጥቃት ዕርምጃውን እቀጥለለሁ ሲሉ ኤርዶዋን ዝተዋል።

800 የሚሆኑ የኩርድ ተዋጊዎች ከድንበሩ አካባቢው ወጥተዋል። ነገር ግን 1,300 የሚሆኑት አልወጡም ይላሉ ኤርዶዋን።

የቱርክ ፕረዚዳንት በዩናይትድ ስቴትስ ግፊት የአምስት ቀናት የተኩስ ማቆም ሥምምነት ማድረጋቸውን መሰረት በማድረግ አሜሪካ ኩርድ ተዋጊዎች ከድንበሩ አካባቢ እንዲወውጡ ግፊት ካላደረገች በስተቀር ጥቃቱን ከቆምንበት ጠንክረን እንቀጥላለን ብለዋል ኤርዶዋን።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG