በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩስ በሶሪያ በድሮን ጥቃት የአልቃይዳ መሪ መግደሏን አስታወቀች


 ፎቶ ፋይል-- ኤም ኪዩ-9 ድሮን
ፎቶ ፋይል-- ኤም ኪዩ-9 ድሮን

የዩናይትድ ስቴትስ የጦር ኃይል ትናንት አርብ ሶሪያ ውስጥ ባደረስው የድሮን ጥቃት አንድ ከፍተኛ የአል ቃይዳ መሪ መገደሉን የዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ ዕዝ ተናገረ።

የዕዙ ቃል አቀባይ ሻለቃ ጆን ሪግስቢ በሰጡት መግለጫ "የአብዱልሃሚድ አልማታር መገደል ሽብርተኛው ቡድን በዐለም ዙሪያ በዩናይትድ ስቴትስ ዜጎች፥ በአጋሮቻችን እና በንፁሃን ሲቪሎች ላይ ጥቃት ለማድረስ ሴራውን የሚቀጥልበትን ዐቅሙን ያሰናክልበታል" ብለዋል።

ከፍተኛው የአልቃይዳ መሪ የተገደለበት የድሮን ጥቃት የተካሄደው ሶሪያ ውስጥ በሚገኝ የዩናይትድ ስቴትስ ኃይሎች የጦር ሰፈር ላይ ከደረሰው ጥቃት ከሁለት ቀን በኋላ መሆኑ ነው። በጥቃቱ በዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮች ላይ የሞትም ሆነ የመቁሰል አደጋ አልደረሰም።

የማዕከላዊ ዕዙ ቃል አቀባይ የድሮን ጥቃቱ ርምጃ የተወሰደው ለዚያ ጥቃት ዐጸፋ ለመመለስ ይሁን አይሁን አልዘረዘሩም።

XS
SM
MD
LG