በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን ጡረታ እወጣለሁ ባሉት የጠ/ፍ/ቤቱ ዳኛ ምትክ የመጀመሪያዋን ጥቁር ሴት እተካለሁ አሉ


ፎቶ ፋይል፦ በዩናይትድ ስቴትስ የ83 ዓመቱ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ስቴፈን ብራየር
ፎቶ ፋይል፦ በዩናይትድ ስቴትስ የ83 ዓመቱ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ስቴፈን ብራየር

በዩናይትድ ስቴትስ የ83 ዓመቱ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ስቴፈን ብራየር በፍርድ ቤቱ የ27 ዓመት አገልግሎታቸው፣ የተራማጁ ወገን ድምጽ ሆነው ከቆዩ በኋላ፣ በጡረታ ለመገለል የወሰኑ መሆኑን ማስታወቀቸው ተገለጸ፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ሚዲያዎች ትናንት እንደዘገቡት፣ ፕሬዚዳንት ባይደን፣ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ፣ ሦስት ወግ አጥባቂ ዳኞችን በመሾም፣ የፍርድ ቤቱ አቋም እንዲያዘነብል ማድረጋቸው ከተነገረ በኋላ፣ ራሳቸው የመረጡትን ሰው ለመተካት እድሉን ያገኙ መሆኑን ተመልክቷል፡፡

ዳኛው በራየር፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የዓመቱ የሥራ ዘመን እስከሚያበቃበት ሰኔ ወር፣ ወይም ባይደን የራሳቸውን ሰው እስኪተኩ ድረስ ሊቆዩ እንደሚችሉ የዜና ምንጮቹ ዘግበዋል፡፡

ባይደን፣ ትረምፕ እንዳደረጉት፣ የሚመርጧቸውን እጩ ዳኞች ዝርዝር ይፋ ባያደርጉም፣ ልክ የመጀመሪዪቱን የጃማይካና የእስያ ዝርያ ያላቸውን ከማላ ኸሪስን፣ የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት አድርገው እንደመረጡት ሁሉ፣ በፍርድ ቤቱም፣ የመጀመሪዪቷን ጥቁር ሴት የሚሾሙ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ የተባሉት ሴት ማን እንደሆኑ ግን አልተገለጸም፡፡

XS
SM
MD
LG