በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን በፅንስ ማቋረጥ ጉዳይ የጠቅላይ ፍ/ቤቱን የውሳኔ ሐሳብ ነቀፉ


ባይደን በፅንስ ማቋረጥ ጉዳይ የጠቅላይ ፍ/ቤቱን የውሳኔ ሐሳብ ነቀፉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:24 0:00

ፕሬዚዳንት ባይደን ከዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሾልኮ ወጥቷል በተባለው ረቂቅ ሰነድ ላይ የተመለከተው የዳኞች አስተያየት እንደ አውሮፓውያን የቀን አቆጣጠር ከ1973 ዓ/ም ጀምሮ ጸንቶ የቆየውን እና "ሮ ቪ ዌድ" ተብሎ የሚጠራውን ጽንስ የማቋረጥ መብት የሚቀልብስ ነው ሲሉ ተቃውሞ አሰሙ፡፡

ምንም እንኳ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በጉዳዩ ላይ ገና ውሳኔውን ያልሰጠ ቢሆንም የዳኞቹን ውስጣዊ ክርክርና አቋም ይፋ አድርጓል የተባለው እና ሾልኮ የወጣው ሰነድ በአገር አቀፍ ደረጃ ክርክር አስነስቷል፡፡

ፕሬዚዳንት ባይደን “ከ50 ዓመት በኋላ ወደ ኋላ ተመልሰን ሴት ልጅ የምትፈልገውን መምረጥ መብት የላትም ስትባል ይህ በትልቁ ያሳስበኛል፡፡" ብለዋል፡፡ የውሳኔው አዝማሚያ መሰማቱን ተከትሎ በሀገሪቱ ዙሪያ የፅንስ ማቋረጥ መብት ደጋፊዎች ሰልፍ አድርገው ታሪካዊውን ውሳኔ ፍርድ ቤቱ እንዳይቀለብስ ጠይቀዋል፡፡

XS
SM
MD
LG