የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስቴር፣ በሁለቱ የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች መካከል ውጊያ በመቀጠሉ፣ መሀል ካርቱም ከሚገኘው ኤምባሲ፣ ዲፕሎማቶችንና ሠራተኞችን ለማውጣት በሚያስፈልግ ጊዜ እገዛ የሚሰጥ ወታደራዊ ኃይሉን በተጠንቀቅ አቁሟል።
በሌላ በኩል፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንክንና ሌሎችም መሪዎች፣ ሁለቱ ወገኖች፣ ቢያንስ እስከ ፊታችን እሑድ የሚዘልቅ የተኩስ አቁም ይደርሱ ዘንድ ግፊት እያደረጉ ነው።
የአሜሪካ ድምፅዋ ከፍተኛ የዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮች ዘጋቢ ሲንዲ ሴይን፣ ከዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያጠናቀረችውን የዘገባውን ዝርዝር ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።