ዩናይትድ ስቴትስ እና ደቡብ ኮሪያ በዚህ አውሮፓውያን ዓመት የመጀመሪያቸው የሆነውን የጋራ ልዩ ኃይል ወታደራዊ ልምምድ አድርገዋል።
የደቡብ ኮሪያ ጦር ዛሬ ዓርብ እንዳስታወቀው እኤአ ጥር 31 የተደረገው ልምምድ የተካሄደው በኮሪያ ድንበር አቅራቢያ በምትገኘው የሰሜን ደቡብ ኮሪያ ፖቼዮን ከተማ ውስጥ ነው።
ዶን ጉ የተባሉት አንድ የደቡብ ኮሪያ መኮንን ለአሜሪካ ድምጽ እንደተናገሩት "የአሁን ልምምድ የደቡብ ኮሪያ እና ዩናይትድ ስቴትስ ልዩ ኃይሎች እንዲቧደኑና እና የተቀናጀ ልዩ ኦፕሬሽን የማካሄድ አቅማቸውን እንዲያጠናክሩ እድል ሰጥቷቸዋል። ወደፊትም በጠላት ላይ የበላይነትን ለመቀዳጀት የልዩ ኃያሎች ወታደራዊ ግዳጆችንን በሚያገሎበቱ ልምምዶች አማካይነት የራሳችንን አቅም ማጠናከሩን እንቀጥላለን፡፡” ብለዋል፡፡
ልምምዱ የተኩስ፣ ልዩ አሰሳ እና ወደ ጠላት ኃይል ሰርጎ የመግባት ልምምዶችን ያካተተ እንደነበር ሲገለጽ የአጋር አካላት በጋራ የሚያደርጓቸውን ወታደራዊ ግዳጆችን ለማጠናከርና በጋራ ለመስራት ያላቸውን አቅም ለማሳደግ ያለመ ልምምድ መሆኑም ተገልጿል፡፡
መድረክ / ፎረም