በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአሜሪካ አውሎ ነፋስ የቀላቀለ ዝናብ ጉዳት አደረሰ


ሚሽጋን ቀኑን በሙሉ በአውሎ ነፋስ ወይም ቶርኔዶ ስተመታ ውላለች፡፡
ሚሽጋን ቀኑን በሙሉ በአውሎ ነፋስ ወይም ቶርኔዶ ስተመታ ውላለች፡፡

በአሜሪካ በመካከለኛው ምዕራብ በኩል ባሉ ግዛቶች ከባድ ዝናብና አውሎ ነፋስ ትላንት ተከስቶ በርካታ ውድመት ማስከተሉ ታውቋል።

ሚሽጋን ቀኑን በሙሉ በአውሎ ነፋስ ወይም ቶርኔዶ ስተመታ ውላለች፡፡ በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት ስለመኖሩ ባይነገርም፣ በርካታ ሕንፃዎች ላይ ግን ውድመት ደርሷል ሲሉ በአካባቢው የሚገኙ የብዙሃን መገናኛ አስታውቀዋል።

በሚሽጋን የታየው ከባድ የአየር ሁኔታ የተከሰተው፣ በኦክላሆማ አንድ ቀን ቀደም ብሉ የነበረው ቶርኔዶ አንድ ሰውን ገድሎ አምስት በሚሆኑት ላይ ደግሞ ጉዳት ካደረሰ በኋላ ነው።

በግዛቲቱ ሰሜናዊ ምሥራቅ በኩል በመኖሪያ ቤቶች ላይ ከባድ ጉዳት ሲደርስ፣ ዛፎችም መውደቃቸውን የአካባቢው የብዙሃን መገናኛና አስታውቀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG