በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ ጉዳይ የተለያየ አስተያየት የሰጡ የአሜሪካ ም/ቤት አባላት


የኒውጀርሲው ዴሞክራት ሴነተር ባብ መንዴዝ እና የተወካዮች ምክር ቤቱ አባል ግሬጎሪ ሚክስ ባወጡት የጋራ መግለጫቸው፣ የአሜሪካ መንግሥት ሰሞኑን ከጣለው የቪዛ ማዕቀብ ጥሩ ጅምር ቢሆንም ሌሎች ተጨማሪ ጠንካራ እርምጃዎች ያስፈልጋሉ፣ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ መሬት የያዘ ውሳኔ ማሳለፍ ይርኖበታል” ሲሉ ማሳሳባቸው ተመልክቷል፡፡ የኦክላሆማ ሪፐብሊካን ሴናተር ጀምስ ማውንቲን ኢንሆፍ፣ ደግሞ፣ በምክር ቤቱ ፊት ለፊት ሰሞኑን በሰጡት መግለጫ፣ የግጭቱን መንስኤና አመጣጥ ያሉትን ምክንያት አስረድተው፣ የአሜሪካ መንግሥት አሸባሪውን ህወሃትና የኢትዮጵያን መንግሥት በእኩል ዓይን ተመልከቶ ያስተላለፈው ውሳኔ ስህተት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሁለቱ የምክር ቤት አባላት ሴነተር ባብ መንዴዝ እና የተወካዮች ምክር ቤቱ አባል ግሬጎሪ ሚክስ ባጋራ ባወጡት የአስተያየት መልእክታቸው “በትግራይ እየተካሄደ ያለው አስቃቂው ጦርነት ወደ ሰባት ወራት የተጠጋው መሆኑን ገልጸው የሚከፈለው ሰአብአዊ ዋጋ እየጨመረ ነው” ብለዋል፡፡

“በሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎች ቆሰለዋል ወይም ተገድለዋል፡፡ በዘፈቀደ የተገደሉ የጅምላ ፍጅቶች ጾታዊና ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች በግዳጅ የሚካሄዱ መፈቀናሎች ሌሎች የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ተፈጽመዋል፡፡” ያሉት ህግ አውጭዎቹ

“ህጻናት ለእስርና ለጉብልበት ብዝበዛ እየተዳረጉ ነው፡፡ የጤና ማዕከላት ትምህርት ቤቶች ዩኒቨርስቲዎች እና የስደተኛ ካምፖች ወይ ተዘርፈዋል ወይ ወድመዋል፡፡ በዚህኛው የአፍሪካ ክፍል የምግብ እጥረት መኖሩ የታወቀ ቢሆንም አሁን ደግሞ ሂደቱ በመስተጓጎሉ ከፍተኛ የረሀብ ምልክት እየታየ ነው፡፡” በማለት ደርሷል ያሉትን አደጋ ዘርዝረዋል፡፡

“ይህ እልቂት ልክ በአንድ የጦርነት አጋጣሚ የተከሰተ ውጤት አድርገን የምንገልጸው አይደለም፡፡ አሁን እያየነው ያለነው በተቀናጀ ዘመቻ ሆን ተብሎ የሚፈጸም እያንዳንዱ ድርጊት ወደ ጦር ወንጀለኛነት ሊያድግ የሚችልና በሰው ልጆች የተፈጸመ ወንጀል ይመስላል፡፡” ብለዋል፡፡

ህግ አውጭዎቹ በመግለጫቸው “የኢትዮጵያ ግዛት በሆነው ሌሎች ክልል ውስጥ እየተፈጸመ ያለው ስቃይም በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በቂ ትኩረት አልተሰጠውም፡፡” ብለዋል፡፡ “ በአገሪቱ ትላልቅ በሆኑ ሁለቱ ብሄሮች በአማራና ኦሮሞ ሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚደርሰው ጥቃትም እየተስፋፋ ነው፡፡ በአገሪቱ ያሉት አነስ ያሉት የብሄረሰብ ክፍሎችም በተመሳሳይ ሁኔታ ለረጅም ጊዜ በመካከላቸው ባለው ሁኔታ ሳቢያ ጥቃት እየደረሰባቸው ነው፡፡ ይሁን እንጂ ከመንግሥት ቁጥጥር ውጭ የሆኑ ታጣቂዎች፣ የመንግሥት የደህንነት አካላት የተከፋፈሉ ሲሆን ተጠያቂነትም የሌላባቸው በመሆኑ ላለው ስቃይና መከራ አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡” ብለዋል፡፡

መጭው የኢትዮጵያ ምርጫን አስመልከቶ ባሰፈሩት አስተያታቸው

“ጥቂቶች መጭው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ነጻና ፍትሃዊ የመሆን እድል ይኖረዋል ብለው እንደሚያምኑ” ገልጸው “እየተስፋፉ ባሉ ግጭቶች ሳቢያ የምርጫ ቁሳቁሶቹ አቅርቦት ችግር በመኖሩ በተለያይቱ የአገሪቱ አካባቢዎች የሚኖሩት ብዙዎቹ ድምጻቸውን መስጠት እንዳይችሉ ያግዳቸዋል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር ተቸዎችና ደጋፊዎቻቸው በእስር ላይ እንዲቆዩ የተደረጉ ሲሆን መንግሥትም ሁልጊዜ ፍትህ የማግኘት ሂደትና መብታቸውን ሲነፍግ ቆይቷል፡፡”

ቁልፍ የሆኑ የተቃዋሚ ፓርቲዎችም እንቅስቃሴዎቻቸው ስለተገደበ ከምርጫው ሂደት ራሱ ራሳቸውን እንዳለ ለማግለል ተገደዋል፡፡ በተጨማሪም ለህዝባዊ ውይይትና ለሚዲያ ተደራሽነት ያለው እድልም ወዲያውኑ የተዘጋ በመሆኑ ፍርሃትና ራስን ሳንሱስር የማድረግ አዝማሚያን ፈጥሯል፡፡ “ ብለዋል፡፡

“ጠቅላይ ሚኒስትር አብይና ገዥው ፓርቲያቸው ብልጽግና፣ ከነሱ በፊት እንደነበረው አምባገነን አስተዳደር፣ ተመሳሳይ መንገድ መከተል እንደፈለጉም ግልጽ አድርገዋል፡፡” ያሉት ህግ አውጭዎቹ “ይህም በአገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ተስፋ ተደርጎበት የነበረውንና በየአምስቱ ዓመቱ የሚደረገውን እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ተስፋ እንዳይኖረው” አድርጎታል ብለዋል፡፡

“የባይደን አስተዳደርም የወቅቱን ሁኔታ ለመከታተል ያሉትን የዲፕሎማቲክ አማራጮቹን ሁሉ አሰማርቷል፡፡ ፕሬዚዳንቱ ምክትል ፕሬዚዳንቷ የውጭ ጉዳይ ምኒስትር የብሄራዊ የደህንነት አማካሪ ከኢትዮጵያና በአካባቢው ካሉ አቻዎቻቸው ጋር ስለትግራዩ ግጭት ፖለቲካዊ መፍትሄ ለማምጣት እየሠሩ” መሆኑን ገልጸዋል፡፡

“አስተዳደሩ ለሰአብዊ እርዳታ እገዛ የሚሆን ወደ 305 ሚሊዮን ዶላር አዲስ የእርዳታ ገንዘብ መለገሱን” አስታውሰው፣ ከዋይት ሀውስ የተላኩ ልዩ መልእከተኞችም የአስተዳደሩን ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች ለመደገፍ በቅርቡ ወደ አፍሪካ መጓዛቸውን ጠቅሰዋል፡፡

“እንዳለመታደል ሆኖ እነዚህ ሁሉ ጥረቶች የቀየሩት ነገር ጥቂት ሲሆኑ ግጭቱ ግን ተባብሶ ቀጥሏል፡፡” በማለት “ የኢትዮጵያ መንግስት መፍትሄ የሚላቸው ነገሮች የማይሰሩ መሆናቸው ግልጽ ቢሆንም፣ በያዘው መንገድ በግትርነት ቀጥሎበታል፡፡ ስለዚህ ለአሜሪካና አጋሮችዋ የአስተዳደሩን የፖለቲካ ስሌት ወሳኝ በሆነ መንገድ መለወጥ የሚያስፈልግበት ጊዜ አሁን ነው፡፡”

“የባይደን አስተዳደር በትግራይ ያለውን ግፍና መከራ ለማስቆም በቅርቡ ያወጣው የቪዛ እገዳ ጥሩ ጅምር ነው ይሁን እንጂ ሌሎች ተጨማሪ ጠንካራ እምርጃዎች ያስፈልጋሉ፡፡” ብለዋል፡፡

“ከሁሉም ነገር በፊት ቀድሞ መደረግ ያለበት የኤርትራ ጦር ከኢትዮጵያ በአስቸኳይ እንዲወጣ ማድረግ ነው፡፡ የባይደን አስተዳደር አንድ ዓይነት አስተሳሰብ ያላቸው አገራት በማስተባበር በኤርትራ መንግሥት ላይ ዓለም አቀፍ የጦር መሳሪያ ማዕቀብ የሚጣልበትን መንገድ መምራት ይኖርባቸዋል፡፡” በማለትም ህግ አውጭዎቹ መክረዋል፡፡

“የባይደን አስተዳደር ለሰአብዊ መብት ጥሰት ተጠያቂ የሆኑትን የኤርትራን ባለሥልጣናት ላይ የኢኮኖሚ ማዕቀብ ማድረግ ይኖርበታል፡፡” በማለት“በኢትዮጵያም በኩል ተሳታፊ በሆኑት ወገኖች ላይ ተመሳሳይ እምርጃ ሊወሰድ ይገባል፡፡ አስተዳደሩ ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ተቋማት ወደ ኢትዮጵያ መንግሥት የሚደረገው እርዳታ እንዳይሰጥ መቃወም ይኖርበታል፡፡” ብለዋል፡፡

ለህዝብ ቀጥተኛ ጥቅም በሚሰጡ አገልግሎቶች፣ እንደ ጤና እና ትምህርት የመሳሰሉት ግን፣ ከማ ቀቡ ነጻ መሆን አለባቸው፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ ተቋማት ግን በትግራይና በሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚፈጸሙ ግፎች እስካሉ ድረስ የተለመደውን ነገር እያደረጉ እንዲቀጥሉ መፈቀድ አይኖርበትም፡፡” ብለዋል ህግ አውጭዎቹ፡፡

“እንዲሁም የኢኮኖሚ ማዕቀቡ ይህን ድርጊት በፈጸሙት፣ ባስተባበሩት፣ ወይም የሰአብአዊ መብጥ ጥሰት እንዳይቆም ያደረጉት፣ የመንግሥት ባለሥልጣናትን ጨምሮ፣ የህወሃት አባላትና ሌሎች ታጣቂ ቡድኖች ላይም ተፈጻሚ መሆን አለበት፡፡”

በተጨማሪም “ሊያስከትለው የሚችለው የተወሳሰበ ነገር መኖሩ ግልጽ ቢሆንም ኢትዮጵያ ላይ የሚጣለው የጦር መሳሪያ ማዕቀብም ከአማራጮቹ ውጭ መሆን የለበትም፡፡” በማለት ሊወሰድ የሚገባውን እርምጃ አመላክተዋል፡፡

በመጨረሻም “ዩናይትድ ስቴትስ አጋር ከሆኑ የአፍሪካ መሪዎች እና በአካባቢው ከሚሰሩት ከተለያዩ ዘርፈ ብዙ ድርጅቶ ጋር፣ የሰብአዊ መብት ጥሰት እንዳይኖር፣ ተአማኒ፣ ግልጽና ተጠያቂነት ያለበት አሰራር እንዲኖር ከማድረግም ውጭ አልፎ መስራት አለበት፡፡ የአፍሪካ ህብረትና ሌሎችም ብሄራዊ ውይይት እንዲኖር ሁኔታዎች የማመቻቸት ሚና ሊጫወቱ ያስፈልጋል፡፡” ብለዋል፡፡

“ኢትዮጵያ በአካባቢው ለረጀም ጊዜና በቋሚነት የዩናይትድ ስቴትስን ጥቅም በመማስጠበቅ ወሳኝ ሚና እንደነበራት የሚታወቅ በመሆኑ የኢትዮጵያ መንግሥት ይህን ያቀረብነውን የመፍትሄ ሀሳብ ይቃወመዋል ብለን አንገምትም፡፡ ይሁን እንጂ ግን እነዚህን ተግባራዊ አለማድረግ ሰላማዊ ዜጎችን ህይወት ዋጋ ያስከፍላል፣ አላስፈላጊ መከራን ያመጣል በሰብአዊ መብት አስከባሪነት ያለንን የቀዳሚነት ዝናም ያሳጣናል፡፡” በማለትም ያላቸውን ስጋት ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻም “ፍላጎታችን እየወደቀ ካለ መንግሥት ጋር በሚደረግ ትብብር አይሳካም፡፡ በአሜሪካ ኢትዮጵያ ግንኑኘት ጉዳት የሚያስከፍለን ዋጋ በምትፈርስ አገር ከምንከፍለው ዋጋ እጅግ ያነሰ ነው፡፡ በጥንቃቄ የሚወሰድ እምርጃ ግልጽ ነው፡፡ ለሰላማዊ የበለጸገችና ዴሞክራቲክ ኢትዮጵያን የሚሆን መፍትሄ አሜሪካ ማሳየት አለባት፡፡ በማለት አስተያየታቸውን ደምድመዋል፡፡

የሴነተር ጀምስ ማውንቲን ኢንሆፍ አስተያየት

የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኢትዮጵያና ኤርትራ መንግሥት ባለሥልጣኖች ላይ ይፋ ያደረገውን የቪዝ ገደቦችን የሚቃወሙ መሆኑን በመግለጽ አስተያየታቸውን የሰጡት ሌላው የምክር ቤት አባል ደግሞ የኦክላሆማው ሪፐብሊካን ሴነተር ጀምስ ማውንቲን ኢንሆፍ ናቸው፡፡ ኢንሆፍ ሰሞኑን በምክር ቤቱ ፊት ለፊት በሰጡት መግለጫቸው

“ከሁሉም በፊት ግልጽ ማድረግ የሚኖብርን ነገር በተለይ የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ላለው ግጭት ሰላማዊ መፍትሄ ከመሻት ውጭ የምንፈልገው ሌላ ነገር አለመኖሩን ነው፡፡” ብለዋል፡፡

“ይሁን እንጂ ግን” አሉ ሴነተሩ “ ይህን አሸባሪ ድርጅት የሆነውን ህወሃት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በእኩል ዐይን እንዲታይ ተደርጓል፡፡ ያ ተቀባይነት የሌለውና ስህተትም ነው፡፡ ሁለቱንም አንድ እንደሆኑ ነገሮች ሁሉ እኩል አድርገን ማየታችን ያስቆጣል፡፡” ብለዋል፡፡

ሴነተሩ በመቀጠልም “መቶ በመቶ እርግጠኛ መሆን እንዲቻልና ማንም ሰው በዚህ ጉዳይ የተሳሳተ ግምት እንዳይኖረው አንድ ነገር ግልጽ እንዲሆን ልናገር፣ ይህ አስቃቂ የሆነው የሰአብዊ መብት ጥሰት በዓለማችን ምንም ስፍራ አይኖረውም፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድም፣ ይህ ድርጊት በመንግሥት ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ገልጸው ድርጊቱን የፈጸሙትም ተጠያቂ እንደሚሆኑ ግልጽ በማድረጋቸው እጅግ በጣም ኮርቻለሁ፡፡ የሚሆነውም ያ ነው፡፡” ብለዋል፡፡

“ኢትዮጵያን እዚህ ምክር ቤት ውስጥ ከኔ በላይ የሚያውቀው የለም” ያሉት ሴነተሩ “ጥንታዊቷንና ነጻነቷን ጠብቃ ስለኖረችው ኢትዮጵያ ታሪክ” እንደሚያውቁ ተናግረዋል፡፡

ቀደም እኤአ በ1970ዎቹ ዓመተ ምህረት ከነበሩት የኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ስርዐት እስከ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከዚያም ወዲህ እስከ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ድረስ ያሉትን ሁኔታዎች አነሳስተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊና በደንብ እንደሚያውቋቸው የተናገሩት ሴነተሩ፣ መለስ እስካረፉበት 2012 ድረስ የዴሞክራሲን ለማስፋፋት መሞከራቸውንና አንዳንድ ለውጦችንም ማምጣታቸውን መስክረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያምም ብዙ ተጨባጭ ነገሮችን ማስመዝገባቸውን ጠቅሰው፣ ከሳቸውም ሆነ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር በተገናኙበት ወቅት፣ አብረው ጸሎት ማድረጋቸውን ጠቅሰዋል፡፡

አሁን ስላለው ሁኔታም ሲያስረዱ፣ “ይህ ሁኔታ እዚህ ደረጃ ላይ እንዴት እንደ ደረሰ ከሥር መሰረቱ ላስረዳችሁ” በማለት ኢትዮጵያን ከጎበኙበት 2005 ጀምሮ የነበረውንም ሁኔታ ዘርዝረው አስረድተዋል፡፡

19 ጊዜ ያህል ወደ ኢትዮጵያ መመላለሳቸውንና ከጠቅላይ ምኒስትሮች፣ ከካቢኔ አባላትና ህግ አውጭዎች፣ የቢዝነስ ሰዎች የእርዳታ ሠራተኞችን በእነዚህ መካከል ካሉ ሰዎች ጋር መገናኘታቸውንም ተናግረዋል፡፡

እኤአ በ2018 አብይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው የተመረጡት ኢትዮጵያን ለ30 ዓመታት ያህል የገዛው ኢህአዴግ ላይ በተነሳ ተቃውሞ መሆኑን ገልጸው፣አብይ አዲስ አመራር በምትፈልግ አገር ወደ ሥልጣን የመጡ ሰው መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

“አብይም እንደ ተመረጡ ገንቢ ለውጦችን ማምጣት ጀምረዋል፣ እርቅ ለማስፈንና ከሁሉም እክሎች በማለፍ ለሊብራል ዴሞክራቲክ ማሻሻያዎችን አምጥተዋል ውጤትም አስመዝግበዋል፡፡ የፖለቲካ እስረኞችንና ጋዜጠኞችን ከእስር ነጻ አውጥተዋል፡፡ ከኤርትራ ጋር ከአስርት ዓምታት ጦርነት በኋላ እርቅ በመማውረዳቸው የኖቤል ተሸላሚ መሆናቸውን” ጠቅሰዋል፡፡

“ኢህአዴግን በበላይነት ይመሩ የነበሩት ከሰሜን የአገሪቱ ክፍል ከትግራይ የሆኑ የህወሃት አባላት ነበሩ” ብለዋል ሴነተሩ፡፡

አያይዘውም “ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከትግራ ክልል አካባቢ የመጡ ሰዎች ብቻ አገሪቱን የሚመሩበት ሥርአት ሳይሆን ሁሉንም ያቀፈ አዲስ መንግሥት ለማቋቋም ሲነሱ ህወህት ደሰተኛ አልሆነም፡፡ ምክንያቱም ለአስርት ዓመታት የያዙትን ስልጣን የለቀቁ መሆኑን ተሰማቸው፡፡ ከኤርትራ ጋር በነበረው የሰላም ስምምነትም ደስተኞች አልነበሩም፡፡ ስለዚህ አሁንም እንደተጎዱ ስለሚሰማቸው ሰላም አይፈልጉም፡፡” ብለዋል፡፡

ሴነተሩ ኢንሆፍ ማብራሪያቸውን በመቀጠል ህወሃቶች “በዚህ የተነሳ እኤአ በ2019 በአዲሱ መንግሥት ውስጥም ሆነ ፓርቲ ውስጥ መሳተፍ የማይፈልጉ መሆኑን በመግለጽ አንዳንድ እርምጃዎችን መውሰድ ጀመሩ፡፡ በተከሰተው የኮረና ቫይረ ወረርሽኝ እንዲተላለፍ የተደረገውን ብሄራዊ የምርጫ ሰሌዳ በመተላለፍ ከሌሎች ክልሎች ተለይተው የክልሉን ፓርላም ለመቆጣጠር በመስከረም ወር የራሳቸውን ምርጫ አደረጉ፡፡”በማለት ተናግረዋል፡፡

ሴነተሩ አያይዘውም “ከዚያም በኋላ ከአሸባሪው ህወሃት ጋር የተባበረው ሚሊሺያ ባላፈው ጥቅምት በመቀሌ አቅራቢያ ያለውን የኢትዮጵያ ሠራዊት ጦር ሰፈር በማጥቃት በዚያ የነበረውን መሳሪያ ዘረፈ፡፡ ይህን ነገር እንደገና ግልጽ ላድርገው የክልሉ ፓርቲ ህወሃት የመንግስትን ጦር ሠርፈር አጠቃ፡፡ መንግሥትም በአግባቡ ምላሹን ሰጠ፡፡” ካሉ በኋላ

“ስለዚህ ከመጀመሪያውም አሸባሪ የነበሩት ወገን በደንብ የታጠቀ ስለነበረ እስካሁን ድረስ የተራዘመውን ውጊያ መልሶ እያካሄደ ነው፡፡” ብለዋል፡፡

“አሁን እየሆነ ያለው ነገር ይህ ነው፡፡” የሚሉት ሴነተር ኢንሆፍ “ መንግስታችን ሁለት በኩል ዓይን መታየት የሌለባቸውን ወገኖች እኩል አስቀምጦ ማየቱ የሚገርመኝ ለዚህ ነው፡፡ አንደኛው የተመረጠ መንግሥት ሲሆን ሌላኛው ሥልጣኑን እንዲያጣ የተደረገ አሸባሪ ቡድን ነው፡፡” ብለዋል፡፡

“የኢትዮጵያ መንግሥት ይህን የተዘገበውን ድርጊት አለመፈጸሙን በግልጽ አስታውቋል፡፡ ድርጊቱ ተቀባይነት የሌለውን መሆኑን ገልጾ፣ ድርጊቱን የፈጸሙትም ተጠያቂ እንደሚሆኑ ተናግሯል፡፡ ስለዚህ እኛ አሜሪካኖች ኢትዮጵያን ማሳተፍና ዛሬ የምናየው ነገር ሁሉ እስካዛሬ ለዓመታት ሲሰራባቸው የኖሩ ድርጊቶች ውጤት መሆኑን መረዳት አለብን፡፡ እነሱ ደህንነቷና አንድነቷ የተጠበቀ ሰለማዊና የተረጋጋች ኢትዮጵያን ለመገንባት እየሠሩ ነው፡፡” በማለት

“ስለዚህ ሰላም እንዴት አድርገው መልሰው ማስፈን እንደሚችሉ እንዴት አድርገን ልንረዳቸው እንደምንችል ልናነጋግራቸው ያስፈልገናል፡፡” ብለዋል፡፡

በመንግሥታቸው ላይ የቪዛ ማዕቀብ መቅጣት ማለት ለዚህ ያበቃቸውን ታሪክን የማናውቅ ወይም በክልሎች መካከል ያለውን ልዩነት ውጤት መሆኑን መገንዘብ የማንችል ያስመልስብናል፡፡” ያሉት ሴነተር ኢንሆፍ፣ በመጨረሻም

“ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይና በኢትዮጵያ ለምትገኙ ወዳጆቻን በሙሉ በቀጥታ ለንግራችሁ የምፈልገው ታሪካችሁን የምናውቅ ሁሉ ከናንተው ጋር መሆናችንን ልገልጽላቸው እወዳለሁ፡፡” በማለት ንግግራቸውን ደምድመዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

በኢትዮጵያ ጉዳይ የተለያየ አስተያየት የሰጡ የአሜሪካ ም/ቤት አባላት
please wait

No media source currently available

0:00 0:14:33 0:00


XS
SM
MD
LG