በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሴነተር ግራሃም እስራኤል ውስጥ ከኔታኒያሁ ጋር ተወያዩ


የዩናይትድ ስቴትስ የህግ መወሰኛው ምክር ቤት አባል ሪፐብሊካኑ ሴናተር ሊንዚ ግራሃም ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ጋር ትናንት ሐሙስ በቴል አቪቭ ተገናኝተዋል፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ የህግ መወሰኛው ምክር ቤት አባል ሪፐብሊካኑ ሴናተር ሊንዚ ግራሃም ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ጋር ትናንት ሐሙስ በቴል አቪቭ ተገናኝተዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የህግ መወሰኛው ምክር ቤት አባል ሪፐብሊካኑ ሴናተር ሊንዚ ግራሃም ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ጋር ትናንት ሐሙስ በቴል አቪቭ ተገናኝተው መክረዋል።

ከስብሰባው በኋላ ግራሃም እና ኔታንያሁ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ የሰጡ ሲሆን ሴናተር ግራሃም ዩናይትድ ስቴትስ ለእስራኤል ያላትን ድጋፍ አረጋግጠዋል።

ግራሃም በንግግራቸው "በዚህ ክልል ለአገራችሁ መረጋጋትን ለማምጣት አሁን የበለጠ ቁርጠኛ ነኝ፡፡ ምክንያቱም የኢራን ዓላማ ከአረቡ ዓለም ጋር ለመቀራረብ የምታደርጉትን ጥረት ማጥፋት ነው ብዬ አስባለሁ" ብለዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ሴነተር እኤአ ጥቅምት 7 ቀን 2023 የሐማስ ታጣቂዎች በእስራኤል ላይ ባደረሱት ጥቃት የደረሰውን ውድመት ባዩበት በክፋር አዛ ኪቡዝ ዙሪያ በመገኘት ተመልክተዋል።

ሪፐብሊካኑ ግራሃም “የኢራንን አስከፊ ቅዠት እውን ለማድረግ” እንዲሁም በእስራኤል እና በአረቡ ዓለም መካከል እርቅ ለመፍጠር ከባይደን አስተዳደር ጋር በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG