በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ም/ቤቶቹ የዩናይትድ ስቴትስን የ28.9 ትሪሊዮን ብድር መጠን አጸደቁ


የዩናይትድ ስቴትስ የህግ መወሰኛው ምክር ቤት የዩናይትድ ስቴትስ የብድር መጠን 28.9 ትሪሊዮን ዶላር እንዲደርስ የሚይዙትን ሁለት ረቂቅ ህጎች ትንናት ሀሙስ አጽድቆ ለፕሬዚዳንት ባይደን ፊርማ የመራው መሆኑ ተገለጸ፡፡

ምክር ቤቱ ውሳኔውን ያሳለፈው 59 ለ35 ሲሆን በምክር ቤቱ የሪፐብሊካኑ መሪ ሚች መካኔልን ጨምሮ 10 የሪፐብሊካን አባላት የሚገኙበት መሆኑን ተመልክቷል፡፡ ሪፐብሊካኖቹ የውሳኔው ተባባሪ የሆኑት ሃገሪቱን ከዕዳ ክፍያ ቀውስ ያድናታል በሚል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የተወካዮች ምክር ቤትም በበኩሉ 221 ለ212 በሆነ ድምጽ ውሳኔውን ያጸደቀ ሲሆን ከዴሞክራቶቹ ጋር የተቀላቀሉ አንድ የሪፐብሊካን አባል ብቻ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

XS
SM
MD
LG