በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዋይት ሐውስ የተገኘውን ኮኬይን ማን እንዳስገባው አልታወቀም


ዋይት ሐውስ
ዋይት ሐውስ

ከአንድ ሳምንት በፊት፣ በዋይት ሐውስ ተገኝቷል፤ የተባለውን የኮኬይን አደንዛዥ ዕፅ አስመልክቶ ሲያደርግ የነበረውን ምርመራ እንዳጠናቀቀ፣ የፕሬዚዳንቱ ጥበቃ አገልግሎት አስታውቋል።

“ሴክሬት ሰርቪስ” በመባል የሚታወቀው፣ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጥበቃ አገልግሎት ዛሬ እንዳስታወቀው፣ ጎብኚዎች ስልካቸውንና ሌሎችንም የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያቸው በሚያስቀምጡበት ሥፍራ የተገኘውን ኮኬይን፣ ማን ሊያመጣው እንደቻለ ለማወቅ ባደረገው ምርመራ፣ ከጥቅሉ ላይ የጣት አሻራ ለማግኘት አለመቻሉን፤ የተገኘውን የዘረ መል ናሙናንም፣ በወቅቱ ከነበሩት ጎብኚዎች ጋራ ለማነጻጸር በቂ እንዳልኾነ ገልጿል።

በመኾኑም፣ ኮኬይኑን ወደ ዋይት ሐውስ ማን ሊያመጣው እንደቻለ ሳይታወቅ መቅረቱን፣ የጥበቃ አገልግሎቱ አስታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG