በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ማይክ ፖምፔዮ ወደ ሪያድ ያመራሉ


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፓምፔዮ
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፓምፔዮ

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፓምፔዮ በሳዑዲ ዓረብያ የነዳጅ ዘይት ማምረቻ ቦታ ላይ ስለተፈፀመው ጥቃት ለመነጋገር ዛሬ ወደ ሪያድ ያመራሉ።

የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣኖች ጥቃቱ የተነሳው ከኢራን ነው ይላሉ። ከፍተኛው የዩናይትድ ስቴትስ ዲፕሎማት ጥቃቱን አስመልክቶ “ስለምንሰጠው ምላሽ” ከሳዑዲ ዓረብያ ጋር ይነጋገራሉ ሲሉ ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ ተናግረዋል።

በኢራን የሚደገፉ የየመን ሑቲ አማፅያን ባለፈው ቅዳሜ በኢራን የነዳጅ ዘይት ማምረቻ ቦታ ላይ ለደረሰው ጥቃት ኃላፊነት መውሰዳቸው የሚታወስ ነው። የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣኖች ግን በተገኘው ማስረጃ መሰረት ሊሆን አይችላም ይላሉ። ግማሽ የሳዑዲ ዓረብያ የነዳጅ ዘይት ምርት በጥቃቱ ወድሟል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG