በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አዲሶቹ ፍልሰተኞች በዩናይትድ ስቴትስ የመጀመሪያቸውን የምስጋና ቀን አከበሩ


አዲሶቹ ፍልሰተኞች በዩናይትድ ስቴትስ የመጀመሪያቸውን የምስጋና ቀን አከበሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:52 0:00

ከመላው ዓለም በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ የሰፈሩ ፍልሰተኞች በዩናትይትድ ስቴትስ የመጀመሪያቸው የሆነውን የምስጋና ቀን በህብረት አክብረዋል፡፡

ከመላው ዓለም የመጡ በመቶዎች የሚቆጠሩ ፍልሰተኞች አዲስ በተቀበለቻቸው ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የምስጋናን ቀን ለማክበር የተሰበሰቡት በህዳር ወር መጀመሪያ ላይ ነው፡፡

አብዛኞቹ ፍልሰተኞች ዓመታዊውን በዓል ሲያከብሩ የመጀመሪያ ጊዜያቸው ነበር፡፡

ከአፍጋን የመጣች ስደተኛ አኒላ ካሪምዜ ሰለዚሁ ስትናገር “እዚህ መጥቼ ከተለያዩ በርካታ ሰዎች ጋር በመሆኔ በጣም ኩራትና ደስታ ተሰምቶኛል፡፡ እጅግ ደስተኞች ከሆኑ ብዙ ሰዎችም ጋር የምስጋንን ቀን በማክበሬ ደስ ብሎኛል፡፡” ብላለች፡፡

በአሜሪካ የምስጋና ቀን በየዓመቱ ህዳር በገባ በሚውለው አራተኛው ሀሙስ ቀን ላይ ይከበራል፡፡

እለቱ እኤአ በ1600ዎቹ መጀመሪያ ላይ አሜሪካ ውስጥ የነበሩ የእንግሊዝ ቅኝ ገዥዎችና የአገሬው ተወላጆች አብረው በመሆን ማዕድ የሚቋደሱበት በዓል ነበር፡፡

በዚህ የተነሳ ከዚያ ወዲህ ብዙዎቹ አሜሪካውያን የተጠበሰ ተርኪና ጣፋጭ ድንች እየተመገቡ በዓሉን ከወዳጆቻቸውና ቤተሰቦቻቸውጋር ተሰብስበው ያከበራሉ፡፡

ለአንዳንዶቹ የአፍጋኒስታን ፍልሰተኞች ተርኪ መመገብ አዲስ ነገር ነበር፡፡

“በጣም ወድጀዋለሁ፡፡” የምትለዋ የአፍጋን ፍልሰተኛዋ ናዚፋ ካሪማዜ “በጣም ጥሩ ምግብ ነው፡፡ ተርኪ ስበላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡” ብላለች፡፡

አዲስ መጤዎቹን ፍልሰተኞች ከአሜሪካ ባህላዊ ልማዶች ጋር ያስተዋወቀውን ዝግጅት ያሰናዳው በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ከሚገኙት የፍልሰተኞች ማስተናገጃ ድርጅት አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ማህረሰብ ልማት ድርጅት ኢሲዲሲ ነበር፡፡

የኢሲዲሲ መስራችና ፕሬዚዳንት የሆኑት ዶ/ር ጸሀዬ ተፈራ “በመሰረቱ የምናጋራቸው ከታላላቅ የአሜሪካ በዓላት አንዱ ከሆነው ጋር ነው፡፡” ብለዋል፡፡

ዶ/ር ጸሀዬ አያይዘውም “እንዲሁም ደግሞ በአካባቢያችን ፍልሰተኞችን የሚያስተናግዱ የተለያዩ የማህበረሰብ አባላት ባህላዊ ምግቦቻቸውን እንዲለዋወጡ ለማድረግ እንሞክራለን፡፡ ሀሳብም ይለዋወጣሉ፡፡ እርስ በርሳቸውም ወዳጅነትን መለዋወጥ ይችላሉ፡፡” ሲሉ የበዓል ዝግጅቱን ጥቅም አስረድተዋል፡፡

ሚና ታሪን እኤአ ከሀምሌ 2022 ጀምሮ በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ቆይታለች፡፡

“በተለይም በዛሬው የምስጋና ቀን ለአፍጋኖች ለሰጡት እርዳታና እና ዛሬ በአፍጋኒስታን እየሆነ ካለው መከራ አንዳንድ የአፍጋኒስታን ዜጎቻችንን እንዲወጡ ያደረጉትን ሁሉ ማመስገን እፈልጋለሁ” ስትልም ካሳላፈችው መከራ በኋላ በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ መሆኗን ታመሰግናለች፡፡

እአአ ነሀሴ 2021 ላይ አፍጋኒስታንን የተቆጣጠሩትን ታሊባኖችን በመሸሽ በሺዎች የሚቆጠሩ አፍጋኖች ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ተሰደዋል፡፡

ብዙዎቹ ፍልሰተኞችም ለዚያ ምስጋናችንን እናቀርባለን ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG