በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ዜጎቿ ወደ ቻይና እንዳይጓዙ አሳሰበች


ፎቶ ፋይል፦መንገደኞች በምዕራብ ቤጂንግ ባቡር ጣቢያ 6/18/2023
ፎቶ ፋይል፦መንገደኞች በምዕራብ ቤጂንግ ባቡር ጣቢያ 6/18/2023

ቻይና ውስጥ በዘፈቀደ በሚፈጸም የህግ ማስከበር ርምጃ፡የመውጫ ቪዛ እገዳ እና ያለ በቂ ሕጋዊ ምክኒያት ለእስር የመዳረግ ዕጣ ሊኖር እንደሚችል በማስጠንቀቅ ዩናይትድ ስቴትስ ዜጎቿን ወደዚያች ሀገር እንዳይጓዙ አሳሰበች።

ለተባሉት አድራጎቶች ስለተጋለጡ ሰዎች የጉዞ ማሳሰቢያው በዝርዝር ባያወሳም አንድ አሜሪካዊ ባለፈው ግንቦት ወር በስለላ ድርጊት ተወንጅሎ የዕድሜ ልክ እስራት እንደተፈረደበት ይታወሳል።

ዩናይትድ ስቴትስ ያወጣችው ይህ ማሳሰቢያ የቻይናን ጥቅም ይጎዳሉ ተብለው በሚታመኑ ጉዳዮች ዙሪያ ሊወሰዱ ስለሚችሉ ርምጃዎች ባለፈው ሳምንት ያጸደቀችውን ብርቱ የውጭ ግንኙነት ሕግ የተከተለ ነው።

ዩናይትድ ስቴትስ ካሁን ቀደምም ወደ ቻይና የሚደረጉ ጉዞዎችን አስመልክቶ ለዜጎቿ ተመሳሳይ ማሳሰቢያዎችን ብታወጣም፣ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የወጡት ማሳሰቢያዎች ግን በዋናነት ከኮቪድ-19 እገዳዎች ጋር የተዛመዱ ነበሩ።

ቻይና በበኩሏ በቅርቡ ያሳለፈችው ሰፊ የጸረ ስለላ ህግ የውጭ አገር ዜግነት ባላቸው የንግድ ማሕበረሰብ አባላት ላይ ከፍተኛ ሥጋት አሳድሯል፡፡ ቢሮዎቻቸው እየተወረሩ ሲሆን እና በውጭ አገር ተቺዎቿ ገደብ ለመጣል የታለመ ህግም ደንግጋለች፡፡

XS
SM
MD
LG