በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዩናይትድ ስቴትስ የተቃውሞ ሰልፉ ቀጥሏል


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ ሚኒያፖሊስ ከተማ በፖሊስ እጅ ባለበት ህይወቱ ማለፉን ተከትሎ በሀገሪቱ ዙሪያ የተቃውሞ ሰልፉ ቀጥሏል፤ የዛሬው የሀገሪቱ መዲና የተቃውሞ ሰልፍ ከሰሞኑ ሁሉ የገዘፈ እንደሚሆን ተጠብቋል፤

የሚኒያፖሊስ ከተማ አስተዳደር ፖሊሶች የሚይዙትን ግለሰብ አንገት አንቀው በቁጥጥር ማዋል እንዲታገድ ተስማምተዋል፤ ፖሊሶች ሌላ ባልደረባቸው ከሚፈቀደው ውጭ ሃይል ሲጠቀም ካዩ ጣልቃ ገብተው እንዲያስቆሙ እና ለሚመለከተው የበላይ አካል እንዲያስታውቁ ግዲታ ለማስገባትም ተስማምተዋል

ጆርጅ ፍሎይድ ነጩ ፖሊስ አንገቱ ላይ በጉልበቱ ቆሞ መተንፈስ አልቻልኩም ብሎ ቢቃትትም ከስምንት ደቂቃ በላይ አንቆ ይዞት ህይወቱ እንዳለፈ ይታወቃል፤

የአርባ ስድስት ዓመቱ ጆርጅ በዚህ ሁኒታ መሞቱን ተከትሎ በሀገሪቱ ዙሪያ ፍትህ በትክክል እንዲተገበር ተቋማዊ ለውጦች እንዲወሰዱ የሚጠይቁ ሰልፎች ሲካሄዱ ቆይተዋል፤

ከአሜሪካም ውጭ ለንደን ፓሪስ እና ሲድኒን ጨምሮ በአያሌ ትላልቅ ከተሞች በብዙ ሺዎች የተቆጠረ ህዝብ የተቃውሞ ሰልፎች አካሂዷል

በተያያዘ ዜና በዋሽንግተን ዲስ ከንቲባ ሙሪየል ባውዘር ፈቃድ ወደዋይት ሃውስ ቤተ መንግሥት በሚወስደው ጎዳና ላይ በድምቅ ብጫ ቀለም ብላክ ላይቭስ ማተር የጥቁሮች ህይወት ክቡር ነው የሚለው መፈክር አስፋልቱ ላይ ተጽፏል፤ አንደኛውን መንገድም ከንቲባዋ ብላክ ላይቭስ ማተር ፕላዛ ሲሉ ሰይመውታል

XS
SM
MD
LG