በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኦፒዮይድስ - የአሜሪካ የወቅቱ ቀውስ


ዩናይትድ ስቴትስ ካሉባት የበረቱ ፈተናዎች አንዱ በወል መጠሪያ ‘ኦፒዮይድስ’ የሚባሉ አደንዛዥና ሕመም አስታጋሽ መድኃኒቶች ሥር የሰደደ ቀውስ ነው።

ዩናይትድ ስቴትስ በአደንዛዥ መድኃኒቶች ዕፅዋትና ቅመማ ቅመም ላይ ጦርነት ካወጀች ግማሽ ምዕት ዓመትን አስቆጥራለች።

አሜሪካ እነሆ እንደገና ከዚያ አደገኛ ሁኔታ ጋር ትንቅንቅ ላይ ነች።

ያለፉ ስህተቶች ምን ነበሩ? ከእንግዲህ እንዳይደገሙስ ምን ማድረግ ይገባል? ኤክስፐርቶች የሃሣብ ገበያ ወጥተዋል።

ፕሬዚዳንት ሪቻርድ ኒክሰን በአደንዛዥ ዕፆችና ቅመማ ቅመም ሕገወጥ ዝውውርና አጠቃቀም ላይ ጦርነት ያወጁት ልክ የዛሬ 46 ዓመት ነበር። ከኒክሰን በኋላም የመጡ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንቶች ሁሉ እያንዳንዳቸው ያንን ጦርነት እየተቀባበሉ ሲያጠናክሩ ቆይተዋል። ፕሬዚዳንት ሮናልድ ሬጋን ‘ያ ጠላት ትውልድ ዘለል’ መሆኑን ተናግረዋል።

ጦርነቱ እጅግ ውስብስብና አስቸጋሪ ነው። ዛሬም ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ያወጁት አዲስ ጦርነት የዚያ ክብደት ምልክትና መገለጫ ነው።

የአሜሪካ የፖለቲካ መሪዎች የአደንዛዥ ዕፆችንና ቅመማ ቅመም ቁጥጥር ተቋማትን ስፋትና ብዛት እንዲጨምሩ ሲያደርጉ ቆይተዋል።

ግዙፎቹን የአደንዛዥ ዕፆችና ቅመማ ቅመም አምራች፣ አሥርጎ አስገቢና አሠራጭ መረቦች ለመበጣጠስ ለታለሙ ወታደራዊ ዘመቻዎች በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ዶላሮች ሜክሲኮና ደቡብ አሜሪካ ውስጥ ፈስሰዋል።

እነዚያ ግዙፍ የድብቅ ዓለም ኩባንያዎች ኮኬይንና ሄሮይንን የመሣሰሉ አደገኛ ቅመማ ቅመምን ጨምሮ እጅግ በርካታ ዓይነትና መጠን ያላቸውን ማደንዘዣዎች በአሜሪካና በዓለም ዙሪያ እያሠራጩ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ትርፎችን የሚያጋብሱ ናቸው።

ኦፒዮይድስ - የአሜሪካ የወቅቱ ቀውስ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:20 0:00

አደንዛዥ ዕፆችን ለመቆጣጠር ለአርባ ዓመታት በተካሄደው ጦርነት የብዙ ሰው ሕይወት ጠፍቷል፤ ወደ አንድ ትሪሊዮን የሚገመት ገንዘብ ወጥቷል።

ጦርነቱ ‘ከሽፏል’ የሚሉ ብዙ ናቸው።

ጦርነቱ “ጥቁሮችና ሂስፓኒኮችን ለእሥር ቤቶች የዳረገ፤ ነጮች በሕክምና እንዲያገግሙ ለማድረግ የሞከረ፤ የዘር ገፅታ የያዘ ነበር” ያሉም አሉ።

አሁን በስፋት እየተሰማ ያለው አዲስ አያያዝ መኖር እንዳለበት የሚመክር ሃሣብ ነው።

አደንዛዥ ዕፆችንና ቅመማ ቅመምን መውሰድን በወንጀል አድራጎትነት ከመፈረጅና ወሳጆቹንም ከማሳደድ ይልቅ ይህንን ‘ጋጠወጥ አጠቃቀም’ ተብሎ የተጠራን ችግር እንደ ‘ኅብረተሰብ ጤና ቀውስ’ መውሰድ ይሻላል የሚለው የሕዝብ አስተሳሰብ እያመዘነ ነው።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ኦፒዮይድስ - የአሜሪካ የወቅቱ ቀውስ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:15 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG