በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰሜን ኮሪያ የአጭር ርቀት ተምዘግዛጊ ሚሳይሎች ትዕይንት


የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዮ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዮ

ሰሜን ኮሪያ ትናንት አከታትላ የተኮሰቻቸው የአጭር ርቀት ተምዘግዛጊ ሚሳይሎች ትዕይንት ከአሜሪካ ጋር የጀመረችውን የኒኩሌር ትጥቋን የማስፈታት ንግግር ሂደት እንደማያጨናግፈው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዮ አስታወቁ።

ፒዮንግያንግ ካስወነጨፈቻቸው ሚሳይሎች ከራሷ ግዛት ያለፈ አንድም አረር እንዳልነበረ የገለፁት ፓምፔዮ የሃገሪቱን የኒኩሌር መርኃግብር ለማስቆም የሚደረገው ንግግር “በስምምነት እንዲቋጭ የሚያስችል ዕድል አሁንም እንዳለ ነው” ብለዋል።

ከሰሜን ኮሪያው ፕሬዚዳንት ኪም ጋር “ስምምነት ላይ እንደርሳለን” የሚል እምነት እንዳላቸው የዩናይትድ ስቴትሱ መሪ ዶናልድ ትረምፕ ትናንት በትዊተር ባሠፈሩት መልዕክት ጠቁመዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG