በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ በሰሜን ኮሪያ ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር መረብ ላይ ያነጣጠረ ማዕቀብ ጣለች


ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ግምጃ ቤት፤ ዋሽንግተን፣ ዲሲ
ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ግምጃ ቤት፤ ዋሽንግተን፣ ዲሲ

ዩናይትድ ስቴትስ መቀመጫቸውን የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ባደረጉ ሁለት ግለሰቦች እና አንድ ድርጅት ላይ ዛሬ ማክሰኞ ማዕቀብ ጥላለች፡፡

በመረጃ ቴክኖሎጂ ሠራተኞች እና በሳይበር ወንጀሎች አማካይነት በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር በመሰብሰብ የሰሜን ኮሪያን መንግሥትን በሚረዳ መረብ እጃቸው አለበት በማለት ወንጅላቸዋለች።

የዩናይትድ ስቴትስ ግምጃ ቤት በአወጣው መግለጫ፣ ማዕቀቡ የተጣለባቸው ሰዎች በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በሚገኝ ኩባንያ በኩል፣ ሕገ ወጥ ገንዘቦችን በመደበቅና ወደክሪፕቶ መገበያያ በመቀየር ለፒዮንግያንግ እንዲደርሱ በማመቻቸት መሳተፋቸውን አስታውቋል፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየት የተጠየቀው በተባበሩት መንግሥታት የሰሜን ኮሪያ ልዑክ ወዲያውኑ ምላሽ አልሰጠም፡፡

ዋሽንግተን ለሰሜን ኮሪያ ጅምላ ጨራሽ የጦር መሣሪያዎች እና የባሊስቲክ ሚሳይል መርሃ ግብሮች የሚሰጥ የገንዘብ ድጋፍ ለማስቆም እየተንቀሳቀሰች መኾኗን የዩናይትድ ስቴትስ ግምጃ ቤት አስታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG