በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአሜሪካ የስድስት ዓመት ፍልስጥኤማዊ ሕፃን ተገደለ


የ71 ዓመቱ አዛውንት ጆሴፍ ቹባ
የ71 ዓመቱ አዛውንት ጆሴፍ ቹባ

በአሜሪካ፤ በኢሊኖይ ግዛት፣ አንድ የ71 ዓመት ነዋሪ፣ የስድስት ዓመት ፍልስጥኤማዊ ሕፃንን፣ 26 ጊዜ በትልቅ ቢላዎ ወጋግቶ እንደገደለው ተነግሯል። የሕፃኑ ወላጅ እናትም፣ በሆስፒታል ለሕይወቷ በሚያሰጋ ኹኔታ ውስጥ እንደምትገኝ ታውቋል።

ፕሌይንሺፕ በተሰኘ ከተማ የሚኖሩ እናት እና ልጅ ፍልስጥኤማውያንን፣ በመኖሪያቸው ሳሉ በቢላዎ የወጋቸው አዛውንቱ ጆሴፍ ቹባ፣ ሃይማኖታቸውንና እየተካሔደ ያለውን የእስራኤል እና ሐማስ ጦርነትን መነሻ አድርጎ ነው፤ ሲሉ መርማሪዎች ገልጸዋል። በሕግ ቁጥጥር ሥር የዋለው ግለሰቡ፣ አምስት ክሦች ተመሥርተውበታል፤ ተብሏል።

አሜሪካውያን በአንድነት፤ እስልምና ጠልነትንና በአጠቃላይ በሌሎችም ላይ የሚታይን ጥላቻ ማውገዝ ይኖርባቸዋል፤”

ሕፃኑ ዋዲያ አል ፋዩሚ በመባል ሲታወቅ፣ እናቱ ደግሞ ሃናን ሻሂን እንደምትባል፣ በቺካጎ የአሜሪካ እስላማዊ ም/ቤት ቅርንጫፍ አስታውቋል። ተከሳሹ ጥቃቱን ከመፈጸሙ አስቀድሞ፣ “እናንተ ሙስሊሞች መገደል አለባችኹ፤” እያለ ሲጮኽ እንደነበር ተመልክቷል።

እናት እና ልጁ፣ የተከሳሹን ቤት የታችኛው ወለል ተከራይተው ይኖሩ እንደነበር ታውቋል። የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ እርሳቸው እና ቀዳማዊት እመቤት ጂል ባይደን፣ በግድያ ድርጊቱ እጅግ መደንገጣቸውን አስታውቀዋል።

“አሜሪካውያን በአንድነት፤ እስልምና ጠልነትንና በአጠቃላይ በሌሎችም ላይ የሚታይን ጥላቻ ማውገዝ ይኖርባቸዋል፤” ሲሉ ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG