ዋሺንግተን ዲሲ —
የዩናይትድ ስቴትስ ጦር እንዳስታወቀው፣ ምሥራቅ አፍጋኒስታን ውስጥ በተካሄደ ውጊያ አንድ ወታደሩ ሲገደል፣ ሌሎች አራት ደግሞ ቆሰሉ። ውጊያው በትናንቱ ዕለት የተካሄደው፣ የፓኪስታን አዋሳኝ በሆነውና አስጊ የፀጥታ ሁኔታ ባለበት ናንጋርሃር ክፍለ ሀገር አችሂን ወረዳ ውስጥ ነው።
ከቆሰሉት ወታደሮች ሁለቱ የአቅራቢያ ሐኪም ቤት እየተረዱና ለሕይወታቸውም በማያሰጋ የጤንነት ሁናቴ ላይ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፣ ሌሎቹ ደግሞ ወደ መደበኛ ሥራቸው እንደተመለሱ፣ ከጦሩ የወጣ መግለጫ አመልክቷል።
በአፍጋኒስታን የዩናይትድ ስቴትስ ኃይሎች ዋና አዛዥ ጀነራል ጆን ኒከልሰን፣ "በሞት በተለየንም ሆነ የመቁሰል አደጋ በደረሰባቸው አባሎቻችን ጥልቅ ኃዘን ተሰምቶናል" ሲሉ ለሰለባዎቹ ቤተሰቦች መልዕክት አስተላልፈዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ