በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሶማሊያ ውስጥ 13 የእስላማዊ መንግሥት ቡድን ተዋጊዎች መገደላቸው ተገለፀ


ዩናይትድ ስቴትስ ሶማሊያ ውስጥ ባደረሰችው የአየር ጥቃት አስራ ሦስት የእስላማዊ መንግሥት ቡድን ተዋጊዎች መገደላቸው ተገለጠ።

የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ዕዝ (አፍሪኮም) ትናንት ሃሙስ ምሽት ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው በጎሊስ ተራሮች አካባቢ በሽብርተኛ ቡድኑ ላይ ጥቃት ተካሂዷል።

ባደረግነው ግምገማ በአየር ጥቃቱ የተገደለም ሆነ የቆሰለ ሲቪል የለም ሲልም መግለጫው አክሎ አመልክቷል። በቅርቡ በተካሄደ ሌላ የዩናይትድ ስቴትስ የአየር ጥቃት ሦሶት የአይ ኤስ ቡድን ተዋጊዎች መገደላቸው ይታወሳል።

አብዱራሂም ዱኩብ የተባለውን በሶማሊያ የኢስላማዊ ቡድን ተዋጊዎች መሪ ገድለነዋል ሲል አፍሪኮም ባለፈው ሚያዝያ ወር አስታውቋል።

ሶማሊያ ውስጥ የሚንቀሳቀሰው ሽብርተኛ ቡድን ግን አይ ኤስ ብቻ አይደለም። ከአልቃይዳ ጋር ቁርኝት ያለው አልሸባብ ሶማሊያ ውስጥ ቁጥራቸው ከ አይ ኤስ የሚበልጥ ተዋጊዎች አሉት ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG