የዩናይትድ ስቴትስ የንግድ ሚኒስትር ጊና ሬይሞንዶ የባይደን አስተዳደር በጥቁር መዝገብ በያዛቸው ድርጅቶች ዝርዝር ውስጥ አዳዲስ የቻይና ኩባንያዎችን ለመጨመር ማሰቡን አስታወቁ፡፡
ሚኒስትሯ ትናንት በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት የዩናይትድ ስቴትስ በቻይና መንግሥት ድጋፍ የተጣሉ ማዕቀቦችን መተላለፍ የሚፈልጉ ድርጅቶችን በመከታተል እየመረመረች መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
በቻይና ውስጥ የሚገኙና በመጥፎ ምግባራቸው በጥቁር መዝገብ ውስጥ የተካተቱ ድርጅቶች የተጣለባቸውን ማዕቀብ ለመተለላለፍ አዳዲስ ስያሜዎችን ይዘው እንደሚመጡም ተመልክቷል፡፡
የቀድሞ ፕሬዚዳንት ትራምፕ አስተዳደር እኤአ የቴክኖሎጂ ድርጅት የሆነውን ሁዋዌን ጨምሮ በበርካታ የቻይና ንግድ ድርጅቶች ላይ ማዕቀብ መጣሉ ይታወሳል፡፡
የባይደን አስተዳደርም ያንኑ ፖሊሲ የገፋበት ሲሆን ባላፈው ህዳር ሌሎች ድርጅቶችን በጥቁር መዝግቡ ውስጥ ማካተቱን አስታውቋል፡፡