በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለሚፈልሱ “ሜክሲኮ ቆዩ” እየተሠራበት ነው


ጥገኝነት ጠያቂዎች፣ በሳንዲያጎ እአአ ሴፕቴምበር 26/2019
ጥገኝነት ጠያቂዎች፣ በሳንዲያጎ እአአ ሴፕቴምበር 26/2019

በትረምፕ አስተዳደር ወቅት ተግባራዊ የተደረገውና ወደ ዩናይትድ ስቴትስ መግባት የሚፈልጉ በአሥር ሺሆች የሚቆጠሩ ፍልሰተኞች ጉዳያቸውን ሜክሲኮ ሆነው እንዲከታተሉ የሚያስገድደው ደንብ በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ቢሻርም የታችኛው ፍርድ ቤቶች ባሳለፉት ውሳኔ ምክንያት ግን ፕሮግራሙን ለመቀጠል ተገድጃለሁ ሲል የባይደን አስተዳደር ባለሥልጣናት ለቪኦኤ ተናግረዋል።

ውሳኔውን ተግባራዊ ለማድረግ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የደረሰበትን ውሳኔ ለታችኛው ፍርድ ቤት ማሳወቅ እንደሚያስፈልገው የአሜሪካ የሃገር ውስጥ ደኅንነት ባለሥልጣናት ተናግረዋል።

የጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ እንቅፋት የገጠመው ቴክሳስ ግዛት ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት በመውሰዱና ፖሊሲው አሁንም ተግባራዊ ሆኖ መቆየቱ ነው።

የባይደን አስተዳደር ባለሥልጣናት ለቪኦኤ እንደተናገሩት ፕሮግራሙ ፍልሰተኞች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አስከትሏል። ፕሮግራሙ ባለፈው ዓመት ሰኔ በይፋ ተሽሮ ነበር።

ፕሮግራሙን ሙሉ ለሙሉ ማስወገድ ተጨማሪ ሰዎች በአሜሪካና በሜክሲኩ ድንበር በኩል ተሻግረው እንዲገቡ ያበረታታል ይላሉ ተቺዎች።

ፕሮግራሙን መልሶ ለማስቀጠል አንድ የበታች ፍርድ ቤት ባለፈው ሰኔ ያሳለፈውን ውሳኔ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውድቅ አድርጓል።

የባይደን አስተዳደር ባለሥልጣናት ለቪኦኤ እንደተናገሩት ባሁኑ ወቅት በፕሮግራሙ ተመዝግበው የሚገኙ ከፍርድ ቤት በሚሰጣቸው ሰነድ ላይ የተቀመጠውን መመሪያ እንዲከተሉ መክሯል።

XS
SM
MD
LG