የኮሎምቢያው ፕሬዝደንት ከአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ጋራ በትዊት ያደረጉት ምልልስ፣ የቡና ሲኒ ማዕበል አስነስቷል።
ፕሬዝደንት ትረምፕ በሕገ ወጥ ስደተኞች ላይ እየወሰዱ ባለው ጠንክራ እርምጃ መሠረት፣ አሜሪካ ወደ ኮሎምቢያ የምትመልሳቸውን ስደተኞችን የሃገሪቱ መንግሥት እንዲቀበል ዋይት ሃውስ ጠንካራ ትዕዛዝ በማስተላለፉ፣ ሊፈጠር የነበረው የንግድ ጦርነት ተገቷል።
የቪኦኤ ዋይት ሃውስ ዘጋቢ አኒታ ፓወል ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።