ነፍሰ ጡሯ ቬንዝዌላዊት ሮዛ ከሃገሯ ተነስታ ዩናይትድ ስቴትስ ድንበር የደረሰችው አራት ወር ሙሉ በእግሯ ተጉዛ ነው።
በብዙ የደቡብ አሜሪካ ሀገሮች እያቆራረጠች የደረሰችው ሮዛ አሁን ግን "ለምን መጣሁ!?!" እያለች ትፀፀታለች።
የቴክሳስ ግዛት ሪፐብሊካን አገረ ገዢ ወደ ዋሺንግተን ዲሲ በአውቶቡስ አሳፍረው ከላኳቸው ፍልሰተኞች አንዷ ስትሆን አሁን ያለችው ዴላዌር ግዛት ውስጥ ነው።
የቬንዝዊላዊቱንና የኑሮ ጓደኛዋን ታሪክ የያዘውን ሪፖርተራችን አላይን ባሮው ያጠናቀረውን ዘገባ ቆንጅት ታየ ለዛሬ አሜሪካና ህዝቧ ፕሮግራም አሰናድታዋለች።