በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የትረምፕ አስተዳደር ፍልሰተኛ ህፃናትን ከወላጆቻቸው መነጠሉ ተገለፀ

የፕሬዚደንት ትረምፕ አስተዳደር ቀደም ብሎ ከነበረው ዕቅድ በብዙ ሺህዎች የሚበልጡ ፍልሰተኛ ህፃናትን ከወላጆቻቸው ሳይነጥል እንዳልቀረ፣ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት መርማሪዎች ይናገራሉ።

የፕሬዚደንት ትረምፕ አስተዳደር ቀደም ብሎ ከነበረው ዕቅድ በብዙ ሺህዎች የሚበልጡ ፍልሰተኛ ህፃናትን ከወላጆቻቸው ሳይነጥል እንዳልቀረ፣ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት መርማሪዎች ይናገራሉ።

የጤናና የሰብዓዊ አገልግሎቶች ሚኒስቴር ዋና መርማሪ እንዳስታወቀው፣ የመንግሥቱ የመዝገብ አያያዝ የተስተካከለ ባለመሆኑ፣ ከወላጆቻቸው የተነጠሉ ህፃናት ቁጥር በትክክል አይታወቅም።

ባለፈው ዓመት፣ በፍርድ ቤት በተሰጠ ትዕዛዝ መሠረት፣ 2,737 ህፃናት ያለ ህጋዊ ፈቃድ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ከገቡ ወላጆችና አሳዳጊዎች መነጠላቸውን ባለሥልጣናት ተናግረዋል።

ይህ አኃዝ፣ ቀደም ሲል እአአ በ2017 ከወላጆቻቸውና አሳዳጊዎቻቸው የተነጠሉትን ብዙ ሺህ ህፃናት እንደማይጨምር፣ ሪፖርቱ አምልክቷል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG