በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካ የኢትዮጵያ ነገር እንደሚያሳስባት ገለፀች


በኢትዮጵያ በሳምንቱ መጨረሻ የተካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎች ጋር በተያየዘ የተነሱ ሁከቶች ክፉኛ እንዳሳሰቡት የዩናይትድ ስቴይትስ መንግስት አስታወቀ። አዲስ አበባ በሚገኘው ኢምባሲውና በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ የወጡ መግለጫዎች በግጭቱ ከሰለፈኞችና ከጸጥታ ባለስልጣናት በኩል ህይወት ማለፉን ጠቅሶ፤ ጉዳት ለደረሰባቸው ሃዘኔታውን አስታውቋል።

አዲስ አበባ የሚገኘው ኢምባሲ ያወጣው መግለጫ፤ በተለይ “ሰልፎቹ የተካሄዱት ያለፈቃድ መሆኑ እንረዳለን፤ እናም ሁሉም ወገኖች በሰላምና ገንቢ በሆነ ውይይት በሰላም ጉዳዩን ለመፍታት የሚሰሩን ሁሉ እንዲደግፉ እናሳስባለን” የሚለው ቃል በማህበራዊ የመገናኛ ብዙሃን ክርክርና ትችት ቀስቅሷል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

አሜሪካ የኢትዮጵያ ነገር እንደሚያሳስባት ገለፀች
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:36 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG