በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ በአፍሪካ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ እና የዲሞክራቲክ ፓርቲው ተፎካካሪያቸው ጆ ባይደን
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ እና የዲሞክራቲክ ፓርቲው ተፎካካሪያቸው ጆ ባይደን

በዩናይትድ ስቴትስ የሚደረገውን፣ ወሳኝ የፕሬዚዳንታዊ፣ እንዲሁም፣ በየደረጃው ያለውን የመንግሥትና የበርካታ ህዝብ ተወካዮችን ምርጫ፣ መላው ዓለም በቅርብ እየተከታተለው ነው፡፡ አፍሪካ ውስጥ ዴሞክራሲ በሰከነባት ደቡብ አፍሪካም እንዲሁ ነው፡፡ የታሪካዊውን ምርጫ ተለዋዋጭ ሂደትና፣ የሚካሄደውን አስደናቂ ድራማ አስመልከቶ በጉዳዩ የተካኑ ጥቂት ጋዜጠኞች፣ የሚያቀርቡትን ትንተና፣ ደቡብ አፍሪካውያን በልዩ ትኩረት እየከታተሉት ነው፡፡ በዚህ ዙሪያ ባልደረባችን አኒታ ፖል ከደቡብ አፍሪካ የሚከተለውን ዘገባ አጠናቅራለች፡፡

የደቡብ አፍሪካው ሪፖርተር ሸርዊን ብራይስ ፒስ፣ ለ12 ዓመታት ካለበት ኒዮርክ ሆኖ፣ አሜሪካንና የአሜሪካን ፖለቲካ፣ ለአገሩ ዜጎች የመተንተን ሥራ ነበረው፡፡ 2020 ግን በኮቪድ 19 ወረርሽኝ የተነሳ፣ እንኳን ለሱ፣ ለብዙ አሜሪካውያን ጋዜጠኞች ሳይቀር፣ ዜናዎችን እየተከታተሉ የመተንተኑን ሥራ አክብዶታል፡፡ ብራይስ ግን ክብደቱ ለአሜሪካ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም መሆኑን ይናገራል፡፡

ከዚህኛው ዋይት ሀውስ የጎደለውን እውነትን ለማግኘት የምናደርገው ጥረት ቀላል አይደለም፡፡ ለምሳሌ ባለፈው ፕሬዚዳንቱ በኮቪድ 19 ከተጋለጡ በኋላ ከፕሬዚዳንቱም ሆነ ከፕሬዚዳንቱ የህክምና ቡድኖች የምናገኘው መረጃ መጥቀስ ይቻላል፡፡ ስለዚህ ትክክለኛውን ነገር የግድ ከዋይት ሀውስ ላይገኝ ስለሚችል ከተለያየ ቦታ ማመሳከር ይኖርብናል፡፡ ፕሬዚዳንቱ ምን አሉ? ያሉት ነገር እውነት ይሆን? እንላለን፡፡ ይህ እዚህ ያለውን የጋዜጠኝነት ሥራችንን ውስብስብ ያደርግብናል፡፡

ብራይስ፣ ምርጫውን አስመልክቶ ብዙ ጊዜ የሚያቀርበው ዘገባ፣ በጥቅሉ በፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሲሆን፣ በዋነኝነት የዩናይትድ ስቴትስና የአፍሪካን ግንኙነት የተመለከት ይሆናል፡፡ አድማጮቹ ለዴሞክራቲኩ ፕሬዚዳንታዊ እጩ፣ ጆ ባይደንን እንደሚያደሉ ይገምታል፡፡ ይህም በአብዛኛው፣ ባይደን ከቀድሞ ፕሬዘዳንት ኦባማ ጋር ባላቸው ግንኙነትና፣ በምክትል ፕሬዚዳንት እጩነት አጋራቸው አድርገው በመረጧቸው ካማላ ኻሪስ የተነሳ እንደሆነ ያምናል፡፡ በዚያ ላይ፣ ብራይስ “ፕሬዚዳንት ትራምፕ አፍሪካን አስመልከቶ የተናገሩት ንቀት የተሞለበት ንግግር በአፍሪካ ተወዳጅ እንዳይሆኑ አድርጓቸዋል፡፡” ይላል፡፡ ብሩክስ ስፔክተር፣ በጆሃንስበርግ የዩናትድ ስቴትስ ዲፕሎማት የነበሩና አሁን ወደ ጸሀፊነት የተቀየሩት ጡረተኛ ናቸው፡፡ በየለቱ በሚወጣው ማቭሪክ ጋዜጣ ላይ፣ ለደቡብ አፍሪካ አንባቢዎች፣ የአሜሪካ ፖለቲካ ትርጉም እንዲሰጥ ለማድረግ እየሞከሩ ነው፡፡ ይህ ምርጫ፣ በሚጽፉበት የጋዜጣ ዓምድ ላይ እንኳ፣ ያልተለመደ ነገር እንዲያደርጉ፣ ያስገደዳቸው መሆኑን ይናገራሉ፡፡ እንዲህ ብለዋል

“ካንድ ወር ገደማ በፊት፣ የዓለም አቀፍ የምርጫ ታዛቢዎች፣ የአሜሪካን ምርጫ ትክክለኛ፣ ግልጽ፣ ነጻና ፍትሃዊ መሆኑን እንዲታዘቡ በአምዴ ላይ በማሳሰብ ጽፌ ነበር፡፡”

ይህ አስተያየት ግን የሳቸው ብቻ አይደለም፡፡ የአፍሪካ ህብረት ባለሥልጣናት፣ የዩናትድ ስቴትስን ምርጫ የሚታዘቡ ልኡካንን ለመላክ፣ ሀሳብ አቅርበዋል፡፡ ምንም እንኳ፣ ሀሳቡ ተግባር ላይ ይውላል ተብሎ ባይታሰብም፣ አንዳንዶቹ አፍሪካ አገራት፣ የየራሳቸውን የተወሰኑ የምርጫ ታዛቢ ቡድኖችን ለመላክ፣ ማቀዳቸውም ተሰምቷል፡፡ የፖለቲካ ተንታኝ የሆኑት ለይስል ሉዎ ቫርዳን ፣ ለማንኛውም “ይህ ምርጫ የአፍሪካ መሪዎች፣ ለወደፊቱ ምን ሊያደርጉ እንደሚችሉ፣ ተጽእኖ ሊያሳድር የሚችል ነው” በማለት እንዲህ ይላሉ፡፡

ይህ የአፍሪካ አገሮችም ሆኑ መንግሥታት ሁል ጊዜም የሚሰማቸው ስሜት ነበር፡፡ አሁን ከአስተሳሰብ ለውጥም በላይ የሆነ የተቀያየረ ነገር አለ፡፡ ሁሉን ነገር አስመልከቶ፣ ለምሳሌ መልካም አስተዳደርንም ሆነ ሌላው ቀርቶ ለኮቪድ 19 የተሰጠውን ምላሽ በሚመለከት ውስጣቸው የሚያስበው ነገር አለ፡፡ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ የተመለከትነው፣ በለጸጉ የተባሉ አገሮች እንኳ ፣ ራሳቸው እየታገሉ መሆኑን ነው፡፡ እኛ እዚህ እንደ ተቸገርነው ሁሉ፣ እነሱም የአስተዳደር ሥርዓታቸው አደጋ ላይ ነው፡፡

ብራይስ ፒስ እንደሚሉት፣ ይህ ዩናይትድ ስቴትስን አስመልከቶ ለሚዘግብ ሰው፣ በጣም አስገራሚ ጊዜ ነው፡፡

“ይህ ለዩናትድ ስቴትስ እንግዳ የሆነ ወቅት ነው፡፡ ያንን ማመን ያለብን ይመስለኛል፡፡ ይህችን በተራራ አናት ሆና የምታንጸባርቅ ከተማን የምርጫ ሂደት ተአማኒነት መጠራጠር፣ በራሱ ብዙ ሰዎችን ለአፍታም ቢሆን ቆም ያደርጋል፡፡ እኔ እንጃ አሜሪካውያን ከዚህ ውስጥ እንዴት አድርገው እንደሚወጡ አላውቅም፡፡ ጥያቄው ከህዳር ሶስት በኋላ ምን ዓይነት አመራር ይኖራችኋል የሚለው ነው? ያ የምንሄድንበትን ቦታ የሚወስን ይመስለኛል፡፡”

ብቻ የትም ሆነ የት፣ አፍሪካ፣ እሚሆነውን እያየች ነው፡፡ እሳቸውም እንዲሁ!!

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ በአፍሪካ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:14 0:00


XS
SM
MD
LG