በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአጋዴዝ ኒጀር የተገነባ የዩናይትድ ስቴትስ የአየር ሰፈር ሥራ ጀመረ


በአጋዴዝ ኒጀር የተገነባ አዲስ የዩናይትድ ስቴትስ የአየር ሰፈር ሙሉ በሙሉ ሥራ ጀምሮ የመጀመርያ በረራ አካሂዷል።

በያዝነው ሳምንት ሰው አልባ የሥለላና የክትትል በረራዎችን እንዳካሄደ የአፍሪካ ኮማንድ ወይም ዕዝ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግሯል።

“በምዕራብ አፍሪቅ ያለውን የደኅንነት አደጋን ለመቋቋም ከአፍሪቃና ከዓለም አቀፍ አጋሮቻችን ጋር እየሰራን ነው” ብለዋል የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ኮማንድ አዛዥ ጄኔራል ስቲቭን ታውንሰንድ። የዚህ የአየር ሰፍር መገንባት በአፍሪካ አጋሮቻችን ላይ ያለንን መተማመንና በቀጠናው ያለንን የጋራ የደኅንነት ጥቅምን ያሳያል ብለዋል።

$110 ሚሎዮን ዶላር የወጣበት የአየር ሰፈር ከባድ ከሚባሉት ቦታዎች አንዱ ነው ብለዋል የኮማንዱ አዛዥ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG