በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻይና ዩናይትድ ስቴትስ ላይ ቀረጥ እንደምትደነግግ አስታወቀች


ቻይና ዩናይትድ ስቴትስ ለወሰደችው እርምጃ ምላሽ ከአሜሪካ ወደ ቻይና በሚላኩት በ $60 ቢልዮን ዶላር በሚገመቱ ዕቃዎች ላይ ቀረጥ እንደምትደነግግ አስታውቃለች።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕረዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ $200 ቢልዮን ዶላር በሚገመቱ ወደ አሜሪካ በሚላኩ ሸቀጣሸቀጥ ላይ ቀረጥ ከፍ የማድረግ እርምጃ ከወሰዱ በኋላ ነው ቻይና የአጸፍ ምላሽ የሰጠችው። በ $300 ቢዮን ዶላር በሚገመቱ ዕቃዎችም ላይ ቀረጥ እንደሚጨመሩ ታውቋል።

የቻይና የገንዘብ ሚኒስትር በገለጹት መሰረት ከ 5 እስካ 25 ከመቶ የሚሆነው የቀረጥ ጭማሪ እአአ ከመጪው ሰኔ አንድ አንስቶ (ከ 18 ቀናት በኋላ ማለት ነው) ተግባራዊ ይሆናል። የቻይና ምላሽ “የዩናይትድ ስቴትስ የብቻ እርምጃንና የንግድ ተከላካይነትዋን ኢላማ ያደረገ ነው ትላለች ቻይና።

“ቻይና ምን ጊዜም ቢሆን ለውጭ ተጽዕኖ አትንበረከክም። ህጋዊ መብታችንና ጥቅማችንን የማስጠበቅ ብቃትና ቁርጠኛነት አለን። አሁንም ቢሆን ዩናይትድ ስቴትስ በግማሽ መንገድ ላይ እንደምትገናኘን ተስፋ እናደርጋለን ብሏል የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG