በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ የቻይና ንግድ ስምምነት


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶንልድ ትረምፕ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶንልድ ትረምፕ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶንልድ ትረምፕ፣ ከቻይና ጋር የአጭር ጊዜ የንግድ ስምምነት መደረጉን ዛሬ ያስታውቃሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተዘግቧል።

ትረምፕ የመጀመርያ ደረጃ ስምምነቱን ትላንት አጽድቀዋል። ቻይና በኦፊሴል የተናገረችው ነገር የለም። ነገር ግን ስምምነት መደረጉ እንደማይቀር አመላክታለች።

ለስምምነት በቀረበው ሀሳብ መሰረት፣ ቻይና በምታስገባቸው እቃዎች ላይ ያለውን ቀረጥ ይቀንሳል። በመጪው እሁድ በተግባር ላይ ሊውል የነበረውን፣ $160 ቢልዮን ዶላር ቀረጥን ያስቀራል።

በልዋጩ ቻይና በርካታ የእርቅ ግልግሎች እንድታደርግ ይጠይቃል። ቻይና በብዙ አስር ቢልዮን ዶላሮች የሚገመቱ፣ የአሜሪካ የእርሻ ምርቶች እንድትገዛ የሚለውን ያጠቃልላል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG