የአሜሪካው ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ በታይዋን ጉብኝት ሊያደርጉ ይችላሉ የሚለው ዜና መሰማት ከጀመረ ጀምሮ በአሜሪካና ቻይና መሃል ውጥረት አይሎ ባለበት በዚህ ወቅት፣ ፕሬዝደንት ጆ ባይደንና የቻይናው አቻቸው ሺ ጂንፒንግ ትናንት ሃሙስ ረዘም ያለ የስልክ ውይይት አድርገዋል።
ናንሲ ፔሎሲ በታይዋን ጉብኝት የሚያደርጉ ከሆነ አሜሪካ “ጠንከር ያለና የማይቀር የአጸፋ እርምጃ ይጠብቃታል” ስትል ቤጂንግ አስጠንቅቃለች።