የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ግጭቱ ወደ ሌሎችም አካባቢዎች እየተዛመተ ይሆን የሚል ስጋት ባየለበት ሁኔታ ውስጥ እስራኤልን ጨምሮ በርካታ ሀገራትን ለመጎብኘት ትንናት ሐሙስ ወደ መካከለኛው ምስራቅ አምርተዋል።
ባላፈው ማክሰኞ በቤይሩት የሐማስ ምክትል ኃላፊ ሳሌህ አል አሩሪ ከተገደሉ በኋላ በእስራኤል እና በሊባኖስ ታጣቂ ቡድን ሂዝቦላህ መካከል ውጥረት ነግሷል። ግጭቱ ወደ ሌሎች አካባቢዎች ሊዛመት ይችላል የሚል ስጋትም ፈጥሯል፡፡
እስራኤል ግድያውን መፈጸሟን አላመነችም ወይም አላስተባበለችም፡፡ ብሊንከን ወደ እስራኤል የተመለሱት በእስራኤል እና በሐማስ መካከል ያለው ጦርነት ሦስት ወር ሊሞላው ትንሽ ሲቀረው ነው፡፡
ሐማስ እስራኤል ላይ እኤአ ጥቅምት 7 ድንገተኛ ጥቃት በማድረስ 1,200 እስራኤላውያንን ከገደለ በኋላ ይህኛው የብሊነክን አራተኛው ጉብኝታቸው ነው፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማቲው ሚለር የውጭ ጉዳይ ምኒስትሩ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ በሚቀጥለው ሳምንት ውስጥ ቱርክን ፡ ግሪክን፡ ዮርዳኖስን ካታርን፡ የተባበሩት የአረብ ኢሚሬቶችን ሳኡዲ አረቢያን እስራኤልን፡ ዌስት ባንክን እና ግብጽን ይጎበኛሉ፡፡ ከየሀገራቱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮችን እና ከሌሎችም ጋር ይወያያሉ፡፡" ሲሉ ትናንት ሐሙስ ተናግረዋል፡፡
ባላፈው ማክሰኞ በቤይሩት የሐማስ ምክትል ኃላፊ ሳሌህ አል አሩሪ ከተገደሉ በኋላ በእስራኤል እና በሊባኖስ ታጣቂ ቡድን ሂዝቦላህ መካከል ውጥረት ነግሷል። ግጭቱ ወደ ሌሎች አካባቢዎች ሊዛመት ይችላል የሚል ስጋትም ፈጥሯል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማቲው ሚለር ብሊነክን “እአአ ከጥቅምት 7 ቀን ጀምረው ያለማቋረጥ ሲያደርጉ እንደነበረው ሁሉ አሁንም ትኩረታቸውን ግጭቱ እንዳይስፋፋ መከላከል ላይ አድርገው ይሰራሉ፡፡ ግጭቱ እንዳይቀጣጠል ለመከላከል ወገኖቹ በክልሉ ያላቸውን ተደማጭነት እንዴት ሊጠቀሙበት ይችላሉ የሚለውን ጨምሮ ምን ማድረግ እንደሚችሉ ይወያያሉ፡፡ ይህ ግጭት ከጋዛ አልፎ ቢዛመት ለእስራኤል፡ ለአካባቢውም ይሁን ለዓለም አይጠቅምም፡፡” ብለዋል፡፡
እስራኤል እኤአ ከጥቅምት 7ቱ ጥቃት በኋላ የሐማስ መሪዎች ለማጥፋት የዛተች ሲሆን በሰሜን ድንበሯ ሊባኖስ በኩል ያለው ጦሯ በተጠንቀቅ እንዲቆም አዛለች፡፡
ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከ22,000 በላይ ፍልስጤማውያን ጋዛ ውስጥ በእስራኤል ተገድለዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ባይደን የሐማስ ጥቃትን ተከትሎ እስራኤል ራሷን የመከላከል መብት እንዳላት በመግለጽ በሰጡት ድጋፍ ጠንካራ ተቃውሞና ትችት ቀርቦባቸዋል፡፡ የፖለቲካ ጠበብት እስራኤል ጦርነቱን በምትመራበት መንገድ ላይ የባይደንም ሆነ የብሊንከን ተጽዕኖ የማሳደር አቅም ተስፋ ያለው አይደለም ይላሉ፡፡
“ከእነዚህ መካከል የመካከለኛው ምስራቅ ፖሊሲ ተቋም ምክትል ፕሬዝዳንት ብራያን ካቱሊስ እንደሚመስለኝ ዩናይትድ ስቴትስን የሆነ አስማታዊ አቅም ያላት አድርጎ የማየት የተሳሳተ አመለካከት አለ፡፡ የተወሰኑ የጦር መሣሪያዎች መላክ ብታቆም፡ ወይም አንዳንዶቹ ሴኔተሮች እንዳሉት እስራኤል ራሷን ለመከላከል ለምታደርገው ጥረት ገንዘብ የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ ቢቆም እስራኤል የተደቀኑባትን ስጋቶች በተለየ መንገድ ታያቸዋለች የሚል የተሳሳተ አስተያየት ያለ ይመስለኛል፡፡” ብለዋል፡፡
በጋዛ እና በዌስት ባንክ ውስጥ ያሉ ሲቪሎችን መጠበቅ እና መርዳት በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንክን የእስራኤል ጉብኝት ውስጥ ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዙ መሆናቸው ተነግሯል፡፡
መድረክ / ፎረም