በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በመወለድ የሚገኝ የዜግነት መብት እንዲቀር ትረምፕ ግፊት እያደረጉ ነው

ፎቶ ፋይል፦ ከቻይና የመጣችው ስደተኛዋ ኤንድ በዜግነት ሥነ ስርዓት ላይ የሦስት ዓመት ወንድ ልጇን እና የዩናይትድ ስቴትስ ባንዲራ ይዛ፤ በኒው ዮርክ የህዝብ ቤተ መፃህፍት፣ ኒውዮርክ ከተማ፣ እአአ ሀምሌ 3/2018
ፎቶ ፋይል፦ ከቻይና የመጣችው ስደተኛዋ ኤንድ በዜግነት ሥነ ስርዓት ላይ የሦስት ዓመት ወንድ ልጇን እና የዩናይትድ ስቴትስ ባንዲራ ይዛ፤ በኒው ዮርክ የህዝብ ቤተ መፃህፍት፣ ኒውዮርክ ከተማ፣ እአአ ሀምሌ 3/2018
ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በመወለድ የሚገኝ የዜግነት መብት እንዲቀር ትረምፕ ግፊት እያደረጉ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:05 0:00

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ “በመወለድ የሚገኝ ዜግነት” በመባል የሚታወቀው የዜግነት መብት’ እንዲቀር ወይም እንዲቋረጥ የሚያደርግ ፕሬዝዳንታዊ ማዘዣ (ትዕዛዝ) ፈርመዋል፡፡ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ1868 የጸደቀው 14ኛው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ አንድ ሰው የወላጆቹ የዜግነት ሁኔታ ምንም ይሁን ምን በዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶች ውስጥ እስከተወለደ ድረስ የዜግነት መብቱን የሚያረጋግጥ ሲሆን የሲቪል መብቶች ዋና አካል ተደርጎ ይታያል፡፡ የፕሬዝደንት ትረምፕ ትዕዛዝ ታዲያ በአስፈጻሚው አካል ሥልጣን እና በሕገ መንግሥት ማሻሻያው ዙሪያ ሕጋዊ እና ፖለቲካዊ ክርክሮች ቀስቅሷል።

የአሜሪካ ድምጿ የኢሚግሬሽን ጉዳዮች ዘጋቢ አሊን ባሮስ ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG