በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን ከሚያዝያ 11 ጀምሮ "ሁሉም አዋቂዎች መከተብ ይችላሉ" አሉባይደን ቨርጂኒያ ውስጥ በሚገኝ አንድ የእምነት ተቋም ውስጥ ክትባት በመወሰድ ላይ የሚገኙትን አሜሪካውያን ሲያነጋግሩ
ባይደን ቨርጂኒያ ውስጥ በሚገኝ አንድ የእምነት ተቋም ውስጥ ክትባት በመወሰድ ላይ የሚገኙትን አሜሪካውያን ሲያነጋግሩ

ዩናይትድ ስቴትስ በያዝነው የሚያዝያ ወር መገባዳጃ ላይ 200 ሚሊዮን አሜሪካውያንን ለማስከተብ ያስቀመጠቸውን ግብ ለማሳከት ተቃርባለች፡፡ የፕሬዚዳንት ባይደን አስተዳደርም በመላው ዓለም ያለውን የኮቪድ 19 ወረርሽን ለመከላከልና ሌሎች አገሮችን የሚያግዝ አስተባባሪ በመሰየም ተጨማሪዎች እምጃዎችን እየወሰዱ ነው፡፡

በዚህ ወር እኤአ ሚያዝያ 19 ወይም በኢትዮጵያ ሚያዝያ 11 ላይ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የሚገኙ አዋቂዎች በሙሉ ከትባቱን መውሰድ እንደሚችሉ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስታውቀዋል፡፡

ይህ ቀደም ሲል ከተቀመጠው የግንቦት 1 ቀነ ገደብ በሁለት ሳምንት አስቀድሞ የመጣ ነው፡፡ አሁን ስላለው የክትባት ሁኔታ ፕሬዚዳንት ባይደን ይህን ብለዋል

"አሁን በየቀኑ በአማካይ 3 ሚሊዮን ክትባቶችን እየሰጠን ነው፡፡ በሳምንት ከ20 ሚሊዮን በላይ ይሆናል፡፡ ቅዳሜ እለት ብቻ ከ4 ሚሊዮን በላይ ክትባቶችን ሰጥተናል፡፡ ከ62 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ሰዎች 150 ሚሊዮን ክትባቶችን በመሰጥት የመጀመሪያዎቹ አገሮች ነን፡፡"

ክትባቶቹን ለማግኘት ሲባል ከሌሎች አገሮች ከመጣው ግፊት የተነሳ ፕሬዚዳንት ባይደን በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ዓለም አቀፉን የኮቪድ 19ን ለመመከት የሚደረገውን ሥራ እንዲያቀናጁ ጌይል ስሚዝን ሾመዋል፡፡

ስሚዝ የዓለም አቀፍ የጤና ኤክስፐርት ሲሆኑ በትርፍነት የተመረቱ ክትባቶች ለሌላው ዓለም እንዲላኩ የሚሟገቱ ናቸው፡፡ እሳቸውም ስለዚሁ ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ

"የአሜሪካ አመራር በጣም ተፈላጊ ነው ይህንንም እንደምናሟላ በጣም እርግጠኛ ነኝ፡፡"

አነስተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸው አገሮች ቻይና ስሪት የሆኑ ክትባቶችንና ከተባባሩት መንግሥታት የጋራ ክትባት መርሃ ግብር ውስጥ ካለው ኮቫክስ የመጡ ክትባቶችን እየወሰዱ ነው፡፡

ባለሙያዎች ደግሞ ዩናይትድ ስቴትስ ትርፍ የሆኑ ክትባቶችን ከመላክም ያለፈ ሥራ መሥራት እንደምትችል ይናገራሉ፡፡

በዓለም አቀፉ ስትራቴጂና ጥናቶች የጤና ፖሊሲ ማዕከል ዳይሬክተር የሆኑት ጄ ስቴፈን ሞሪሰን እንዲህ ይላሉ

"የክትባቱ ምርት በታቀደው መሠረት እንዲጨምር ይረዳሉ፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃም፣ አሁን ያለውን፣ ተጠያቂነት በጎደለው መንገድ በድብቅና በቀውስ የተሞላውን የክትባቱን ስርጭት አሰመልከቶ ግልጽነት እንዲኖረው ያደርጋል፡፡"

ባለፈው ማክሰኞ ፕሬዚዳንት ባይደን ቨርጂኒያ ግዛት በሚገኘው ቻፕል ውስጥ የሚገኘውን የክትባት መስጫ ጎብኝተዋል፡፡ አሰተዳደራቸውም ክትባቱን ለመውሰድ የሚያቅማሙትን ለማግባባት ከእምነት እና ማህበረሰባዊ ተቋማት ጋር የተጣመረ ህብረት መስርቷል፡፡

የህዝብ አስተያየት መቀበያ ድምጽ እንዳረጋገጠው ክትባቱን ላለመውሰድ የሚያቅማሙት ወደ 20 ከመቶ ይደርሳሉ፡፡

ባይደን ከሚያዝያ 11 ጀምሮ ሁሉም አዋቂዎች መከተብ ይችላሉ አሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:37 0:00

አሜሪካውያን የጤና መመሪያውን የሚጥሱ አሜሪካውያን እየጨመሩ መሆኑን የተነገረ ሲሆን በዚህ ሳምንት በተጀመረው የኮሌጅ ቅርጫት ኳስ ጨዋታዎቹ ብዙዎቹ ተገኝተዋል፡፡

ከቨንደር ቢልት ዩኒቨርስቲ የህክምና ክፍለ ትምህርት ዊሊያም ሻፍነር እንዲህ ይላሉ

"በየቀኑ በቫይረሱ የተያዙ ከ60 ሺ በላይ አዳዲስ ሰዎችን እየተመዘገቡ ነው፡፡ አዋቂ ወጣቶችም ዋነኞቹ የቫይረሱ አስተላላፊዎች ሆነዋል፡፡ ወደ ስፖርት ማዘውተሪያዎች ይሄዳሉ፡፡ ወደ ምግብ ቤቶችና መጠጥ ቤቶችም እየሄዱ ነው፡፡"

ዋይት ሐውስ እንደሚለው በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ 40 ከመቶ የሚሆኑን አዋቂዎች ቢያንስ አንደኛውን ዙር ክትባት ወስደዋል፡፡ 20 ከመቶ የሚሆኑ ዜጎችም ሙሉ ለሙሉ ተከትበዋል፡፡

(የዋይትሐውስ ዘጋቢ ፓትሲ ውዳክስዋራ ከላከቸው ዘገባ የተወሰደ፡፡)

XS
SM
MD
LG