በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጄፍሪ ፌልት ማን ዛሬና ነገ አዲስ አበባ ይቆያሉ


ጄፍሪ ፌልት ማን ዛሬና ነገ አዲስ አበባ ይቆያሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:58 0:00

የትግራይ ክልል አማጺያን ኃይሎች የፌደራል መንግስቱ መቀመጫ ወደሆነችው አዲስ አበባ እየገፉ መሆኑን ባስታወቁበት እና የኢትዮጵያ መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ባወጀበት በዚህ ጊዜ፤ የዩናይትድ ስቴትስ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ጄፍሪ ፌልት ማን ዛሬ ሃሙስና ነገ አርብ በአዲስ አበባ ቆይታ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በሌላ በኩልም የኬንያው መሪ ከበፍተኛ ደረጃ ተባብሶ የአገሪቱን ማህበረሰባዊ መስተጋብር ወደ ሚያናጋበት ደረጃ ተሸጋግሯል፡፡” ያሉትን የኢትዮጵያ ግጭት እንዲቆም ጠይቀዋል፡፡

“የግጭቱ መነሻ ምክንያት የቱን ያህልም እንኳ የመረረ ቢሆን ካሁን በኋላ መላውን አገር ለሚያቀጣጥለው እልቂት ስቃይና ግድያ ተቀባይነት ያለው ምክንያት መሆን አይገባውም፡፡” በማለት ሁሉም ወገኖች ችግሮቻቸውን በንግግር እንዲፈቱ አሳስበዋል፡፡

//ዘገባው በአሜሪካ ድምጽ ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ዘጋቢ ሲንዲ ሴን የተጠናቀረ ነው//

XS
SM
MD
LG