በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሶማሊያ ውስጥ የእስላማዊ መንግሥት ደጋፊ ታጣቂዎች ተገደሉ


የዩናይትድ ስቴትስ የጦር ኃይል በትናንትናው ዕለት ሶማሊያ ፑንትላንድ ክፍለ ግዛት ውስጥ የአየር ጥቃት አካሂዶ ሰባት የእስላማዊ መንግሥት ደጋፊ ታጣቂዎች መግደሉን አስታወቀ።

ቪኦኤ ያነጋገራቸው የአካባቢው ባለሥልጣናትና ዕማኞች በሰጡት ቃል ከቦሳሶ በስተደቡብ ምስራቅ እንድ መቶ አርባ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ቲሚርሺ የሚባል ተራራማ አካባቢ የፑንትላንድ ወታደሮች በታጣቂዎቹ ምሽጎች ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን ገልጸዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የጦር ሃይል የአፍሪካ ዕዝ ዛሬ ባወጣው መግለጫ የአየር ጥቃቱን ያካሄድነው ታጣቂዎቹ በአጋር ኃይሎች ላደረሱት ጥቃት አጸፋ ለመመለስ ነው ብሏል።

የፑንትላንድ ኃይሎች በየብስ ባደረሱት ጥቃት ሃያ የአይሲስ ታጣቂዎችን ገድለናል ብለዋል።

XS
SM
MD
LG