በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብሊንከን አፍሪካን በድረ ገጽ መጎብኘት ጀመሩ


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን በአፍሪካው የድረ ገጽ ጉብኝታቸው ከናይጄሪያው ፕሬዚዳንት ጋር ተገናኝተዋል
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን በአፍሪካው የድረ ገጽ ጉብኝታቸው ከናይጄሪያው ፕሬዚዳንት ጋር ተገናኝተዋል

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን በአፍሪካ የጀመሩትን ታሪካዊ ጉዞ ቀጥለዋል፡፡ እንደእውነቱ ከሆነ ካሉበት ቦታ አልተንቀሳቀሱም፡፡ ብሊንከን የመጀመሪያውን የአፍሪካ ጉዟቸውን ያደረጉት በድረገጽ አማካይነት ሲሆን ስድስት ሁነቶችና ስብሰባዎች ላይ በአህጉሪቱ ከፍተኛ ተሰሚነት ያላቸውን እንደ ኬንያና ናይጄሪያ ያሉት አገራት መሪዎችን አነጋግረዋል፡፡

ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶችን በመልካም አስተዳደሮች አማካይነት ማስከበር፣ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ መሰረት ነው፡፡

በትናንቱ የማክሰኞው የመክፈቻ ንግግራቸው ብሊንከን የአሜሪካ መንግስት ምሩቃን ለሆኑ የአፍሪካ ወጣቶች ተነሳሽነት አመራር አባላት አበክረው የተናገሩት በእነዚህ ጉዳዮች ዙሪያ ነበር፡፡

ይሁን እንጂ እሳቸው “አስር ጥያቄዎችን ከቶኒ ጋር” ብለው የሰየሙት የሀሳብ ልውውጥ በድረ ገጽ የተወሰነው ውይይት ቢሆንም ወጣቶቹን ጥያቄ ከማቅረብ አላገዳቸውም፡፡

ብሊንከን አፍሪካን በድረ ገጽ መጎብኘት ጀመሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:41 0:00


አፍሪካውያኑ ወጣቶች አዲሱን ከፍተኛ የአሜሪካ ዲፕሎማት በአየር ንብረት ለውጥ እንዲሁም አፍሪካ ላይ እየተስፋፋች ስላለችው ቻይና ጨምሮ በርካታ ጥያቄዎችን አቅርበውላቸዋል፡፡

ብሊንከን በጥቅሉ የሰጡት መልስ ይህን ይመስል ነበር

“ከአጋሮቻችን ጋር በአፍሪካ ሰላምና ደህንነትን ለማስፈን በቁርጠኝነት እንሰራለን፡፡ አንዳንድ ጊዜ በአጭር ጊዜ ውስጥ የምናደርገው በደህንነት ትብብር እና የሰአብአዊ መብቶች ጥበቃ ዙሪያ በምናደርገው ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች ላይ ያተኮረ ይሆናል፡፡ የመጨረሻው ግባችንና እኛ በጣም ማድረግ የምንፈልገው፣ አገሮች የዴሞክራሲ ተቋሞቻቸውን ሊያጠናክሩ በሚችሉበት መርዳት፣ ለሰዎች የተሻለ ህይወት እንዲመጣ የኢኮኖሚ እድገት እንዲኖር ማድረግ ነው፡፡ በመሠረቱ ማድረግ የምንፈልገው ይህን ነው፡፡”

በድረ ገጽ የተካሄደው የርቀት ጉብኝት ብሊንከን በዋሽንግተን ዲሲ ከሚገኘው ቢሯቸው ሆነው የጊዜ ገደብ ሳያግዳቸው በርቀት እንዲጓዙ አስችሏቸዋል፡፡

ከስብሰባው በኋላ ከያሊ የቀድሞ ተመራቂ ወጣቶች ጋር ያደረጉትን ውይይት አጠናቀው ያመሩት ወደ ናይጄሪያ ነበር፡፡ እዚያም ከናይጄሪያ ፕሬዚዳንትና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያይተዋል፡፡

ከ90 ደቂቃዎች በኋላም ወደ ኬንያ በማምራት በተመሳሳይ ከአገሪቱ ፕሬዚዳንት እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያይተዋል፡፡

ከሁለቱም አገሮች ባለሥልጣናት ጋር የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለማስወገድ ስለሚደረገውም ጥረት ተነጋግረዋል፡፡

በውይይታቸው መካከልም፣ ትልቁ መነጋገሪያ ጉዳይ ስለሆነውና፣ ወደ አፍሪካ በመገስገስ ላይ ስለምትገኘው የዩናይት ስቴትስ ትልቋ ባላንጣና ተቃናቃኝ ስለሆነችው ቻይናም ጉዳይ ከማንሳት ብሊንከን ወደ ኋላ አላሉም፡፡

እንዲህ ብለዋል፤

“የአፍሪካ አገሮች በተለያዩ ዘርፎች ከቻይና ወይም ከፈረንሳይ ከቱርክ ወይም ከብራዚል ወይም ከዩናይትድ ስቴትስና ከሌሎች ጋር ትብብር ሊመሰርቱ ይችላሉ መመስረትም አለባቸው፡፡ ተስፋ የማደርገው ግን የአፍሪካ አገሮችና አፍሪካውያን የማህበረሰብ አባላት እንደዚያ ያሉ ትብብሮችን ሲመሰሩት አይናቸውን በስፋት እንዲከፍቱ ነው፡፡ እውነት ነው ቻይና ዓለም አቀፍ ተፎካካሪ መሆኗ ጥሩ ነገር ነው፡፡ በፍትሃዊ በሆነና አግባብነት ባለው መንገድ ከሆነ የሚደገፍ ነው፡፡ ግን እንደምናየው ከሆነ አስተዳደርን በሚመለከት እኛ ያለን አመለካከት የተለየ ነው፡፡ በቢዝነስም ያለን አቀራረብና አመለካከት የተለየ ነው፡፡ በደህንነትም እና በሌሎች መሰረታዊ ነገሮች ላይ ያለን አቋም እንዲሁ ሲሆን በእነዚህ ጉዳዮች ላይ አንዳንዴ የሚኖረን ትብብር የተለየ ነው፡፡”

በዚህ ጉብኝታቸው በአጭር ጊዜ ውስጥ በማደግ ላይ በምትገኘው አፍሪካ፣ በርካታ አገሮችን በማካለል፣ ብሊንከ ከሳቸው በፊት የነበሩት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችን በሙሉ ቀድመዋል፡፡

በቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር የነበሩት ሁለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አፍሪካን የጎበኙት እያንዳንዳቸው አንድ ጊዜ ብቻ ነው፡፡

ብሊንከን ረዳቶች ይህ ጉብኝት የመጨረሻው አለመሆኑን ይናገራሉ፡፡

የወረርሽኙ ሁኔታ አስተማማኝ ሲሆንም እንደገና በአካል ተገኝተው አህጉሪቱን እንደሚጎበኙም ጨምረው ገልጸዋል፡፡

ብሊንክም እንዳሉት ሁሉንም ነገር ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ማድረግ እንደሚፈልጉ ገልጸው፣ የወጣቱን የዓለም ህብረሰተሰብ ክፍል ድምጽ ማድመጥ እንደሚፈልጉ በመናገር እንዲህ ብለዋል

“እጅግ አስፈላጊ የሆነው ዋናው ነገር፣ አዳዲስ ድምጾችን የወጣቶችን አዳዲስ አመለካከትና ሀሳቦችን መስማት ይኖርብናል፡፡ በሀሳብ ላይ ማንም የበላይነትና ጠቅላይነት የለውም፡፡ ጥሩ ሀሳቦች ሁሌም ተመራጮች ናቸው፡፡ ወደ ሀሳብ ገበያው እነዚህን ሀሳቦች እስካፈለቃችኋቸው ድረስ የሀሳብ ገበያውን ያጥለቀልቀዋል፡፡ ወደ እድገት የሚያመራንም እሱ ይመስለኛል፡፡”

“አፍሪካ ሆይ!” አሉ ብሊንከን “ዩናይትድ ስቴትስ እያደመጠችሽ ነው!

(የቪኦኤ ዘጋቢ አኒታ ፓወል ፖወል ከጆሀንስበርግ ከላከችው ዘገባ የተወሰደ)

XS
SM
MD
LG