በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ጥቃት በአፍጋኒስታን

ፕሬዚዳንት ባይደንና ባለቤታቸው ጂል ባይደን ዛሬ እሁድ በቦምብ ጥቃቱ ህይወታቸን ያጡትን 13 አሜሪካውያንን አስክሬን ለማክበርና ከቤተሰቦቻቸውም ጋር ለመገናኘት ደለዌር በሚገኘው የአየር ኃይል ጦር ሰፈር ተገኝተዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ባይደንና ባለቤታቸው ጂል ባይደን ዛሬ እሁድ በቦምብ ጥቃቱ ህይወታቸን ያጡትን 13 አሜሪካውያንን አስክሬን ለማክበርና ከቤተሰቦቻቸውም ጋር ለመገናኘት ደለዌር በሚገኘው የአየር ኃይል ጦር ሰፈር ተገኝተዋል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ በዛሬው እለት በአፍጋኒስታን ካቡል አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ፣ የፍንዳታ አደጋ ለማድረስ ተዘጋጅቷል የተባለውን ተሽርካሪ፣ ከአየር ላይ በተሰነዘረ ጥቃት ማውደሟን አስታውቃለች፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ ሚኒስቴር፣ ማዕከላዊ ማዘዣ ጣቢያ ቃል አቀባይ፣ ቢል አርባን በዛሬው መግለጫቸው ፣ “ከተሽርካሪውን የተሰማው ሁለተኛው ፍንዳታ፣ ተሽከርካሪው በውስጡ የሚፈነዱ በርካታ ፈንጅዎችን ጭኖ የነበረ መሆኑን ያሳያል፡፡ ስለዚህ ኢላማችን በትክክል ውጤታማ እንደነበር እርግጠኞች ነን” ብለዋል፡፡

ፕሬዚዳን ጆ ባይደን ከጥቃቱ አስቀድመው ትናንት በሰጡት መግለጫ ፣ በሚቀጥሉት 24 እና 26 ሰዓታት ውስጥ፣ በአፍጋኒስታን ካቡል ፣ሌላ ጥቃት ሊሰነዘር ይችላል ሲሉ ያስጠነቀቁ ሲሆን፣ ከሰዓታት በኋላም በካቡል ያለው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲም አደጋው እንደሚደረግ ከታመነ ምንጭ በማረጋገጡ በአውሮፕላን ማረፊያው የሚገኙ ዜጎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ አስጠንቅቋል፡፡

ማስጠንቀቂያው የመጣው ባለፈው ሀሙስ በካቡል አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ በደረሰው የቦምብ ጥቃት 13 አሜሪካውያንና 170 የአፍጋን ዜጎች መገደላቸውን ተከትሎ ነው፡፡

ፕሬዚዳንት ባይደንና ባለቤታቸው ጂል ባይደን ዛሬ እሁድ በቦምብ ጥቃቱ ህይወታቸን ያጡትን 13 አሜሪካውያንን አስክሬን ለማክበርና ከቤተሰቦቻቸውም ጋር ለመገናኘት ደለዌር በሚገኘው የአየር ኃይል ጦር ሰፈር ተገኝተዋል፡፡

ከትናንት በስቲያ ጥቃቱን ባደረሱ፣ የአይሲስ ኬ ሁለት ከፍተኛ አባላት መገደላቸውንና አንድ መቁስሉን፣ የዩናይትድ ስቴትስ መካለከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ፕሬዚዳንት ባይደንም አጥፊዎችን እያደኑ መቅጣቱ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡

አሜሪካውያንና ረዳቶቻቸውን አፍጋኒስታንን ከአገር ለማሰወጣት የተቀመጠው ቀነ ገደብ በሁለት ቀን ውስጥ እንደሚጠናቀቅ በተነገረበት በዚህ ወቅት እስከዛሬው ድረስ ከ114ሺ ሰዎችን ማስወጣት መቻሉን ዋይት ሀውስ አስታውቋል፡፡

XS
SM
MD
LG