በቅርቡ ሾልኮ በወጣው የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞችን አስተያየት የያዘ ሰነድ መሰረት በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሴቶች ጽንስ የማቋረጥ ሕጋዊ መብት የሰጠውን “ሮቪዌድ” የተሰኘውን ውሳኔ በመጪዎቹ ጥቂት ወራት ውስጥ ሳይቀለብሰው እንደማይቀር ይጠበቃል። ይህ ከሆነ ጽንስ የማቋረጥ ጉዳይ በእያንዳንዱ ክፍለ ሀገር የሚወሰን ይሆናል።
ስድስት ሳምንት የሞላውን ጽንስ ማስወረድ በሕግ ክልክል ከሆነባት ከቴክሳስ ክፍለ ሀገር ዳያና ሚችል ለቪኦኤ ያጠናቀረችውን ሪፖርት ቆንጅት ታየ ወደ አማርኛ መልሳዋለች።