በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ ዩክሬን ልቪቭ ከተማ ላይ ብዛት ያለው ሚሳይል ተኩሳለች

ሩሲያ ምዕራብ ዩክሬን ልቪቭ ከተማ የአውሮፕላን ጣቢያ አቅራቢያን ዒላማ ያደረጉ በርካታ ሚሳይሎች ተኩሳለች።

በአውሮፕላን ጣቢያው ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ የከተማዋ ከንቲባ ገልጸው የአውሮፕላን ጥገና ክፍል ግን ተጎድቷል ብለዋል። ዩክሬንን ከፖላንድ ጋር ከሚያዋስነው ድንበር ሰማኒያ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው አካባቢ ላይ በደረሰው ጥቃት በሰው ላይ ምን ያህል ጉዳት እንደደረሰ ለጊዜው የተገኘ መረጃ የለም።

በትናንትናው ዕለት በሩስያ ጥቃት በተመታው የማሪዮፖሉ ህፃናትን ጨመሮ ብዙ መቶ ሰላማዊ ሰዎች የተጠለሉበት የትያትር ቤት ከጥቃቱ የተረፉ ሰዎች እየወጡ ናቸው። ምን ያህሉ በህይወት እንደተረፉ አልታወቀም።


XS
SM
MD
LG