በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩክሬኑ ጦርነት ከጀመረ 100 ቀን ሞላው


የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዶሚር ዘለንስኪ
የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዶሚር ዘለንስኪ

የሩሲያ እና የዩክሬን ጦርነት ዛሬ 100ኛ ቀኑ ሲሆን የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዶሚር ዘለንስኪ የሩሲያ ኃይሎች ከዩክሬን ግዛት ሃያ ከመቶውን ተቆጣጥረዋል ብለዋል፡፡ ዜለንስኪ ለለክሰንበርግ ፓርላማ ባደረጉት ንግግር የሩሲያ ኃይሎች መላዋን ኔዘርላንድስን የሚያክል ግዛት ይዘውብናል ብለዋል፡፡

ሩሲያ ወረራውን ከጀመረችበት ጊዜ ወዲህ ምን ያህሉን ግዛት እንደተቆጣጠረች አልገለጹም፡፡ሞስኮ ክራይሚያን እአአ በ2014 የያዘች ሲሆን በሩሲያ የሚደገፉ ተገንጣዮች ደግሞ የምስራቅ ዩክሬንን ዶንባስ ክፍለ ግዛት አካባቢዎች ከወረራው በፊት መቆጣጠራቸው ይታወሳል፡፡ በአሁኑ ወቅት ከባዱ ውጊያ እየተካሄደ ያለው ዶንባስ ላይ ነው፡፡

ትናንት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ለዩክሬን የሩሲያን ወርራ የምትመክትበት የ700 መቶ ሚሊዮን ዶላር የተራቀቁ የሮኬት አና ሌሎችም መሣሪያዎች ዕርዳታ እንሰጣለን ሲሉ አስታውቀዋል፡፡ ዋይት ኃውስ እንዳለው ዩክሬን ሮኬቶቹን ወደ ሩሲያ ግዛት ውስጥ እንደማትተኩስ ቃል ገብታለች፡፡

ከመሳሪያ ዕርዳታው በተጨማሪ ሌላው ጥሩ ዜና የአውሮፓ ህብረት በሩሲያ ላይ ስድስተኛውን እና በዋናነት ነዳጅ ዘይቷን የሚመለከተውን ማዕቀብ ተግባራዊ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ነው ያሉት የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት በኪየቭ ሙሉ በሙሉ ስራቸውን የሚጀምሩ ኤምባሲዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

XS
SM
MD
LG