በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አቶ ደመቀ መኮንን ከቲቦር ናዥ ጋር ተወያዩ


አቶ ደመቀ መኮንን እና ከቲቦር ናዥ
አቶ ደመቀ መኮንን እና ከቲቦር ናዥ

የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ዛሬ ከአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ሚኒስትር ጋር በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

አቶ ደመቀ የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ክልል እያካሄደ ስለሚገኘው የህግ ማስከበር ዘመቻ ለቲቦር ናዥ ገለፃ አድርገዋል።

የህወሓት ወታደራዊ አቅም ሲጠፋ፣ ጥቃት የተፈፀመባቸውን የመከላከያ ሰራዊት አባላት ነፃ ሲወጡ እና በክልሉ የህግ የበላይነት ሲረጋገጥ ዘመቻው እንደሚያበቃ ለአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ሚኒስትር ቲቦር ናጂ ገልፀዋል።

አቶ ደመቀ በትግራይ ክልል መንግሥት ስላወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና ከአዋጁ ጋር ስለተያያዙ ሥራዎችም ገለፃ አድርገዋል።

እንዲሁም የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በስኬት በመጠናቀቁም አቶ ደመቀ የተሰማቸውን ደስታ ለቲቦር ናዥ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ሚኒስትር ቲቦር ናዥ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ሰላም በቀጠናው ሰላምን ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል፤ የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት።

XS
SM
MD
LG