በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አል-ዛዋሂሪ አፍጋኒስታን እንደነበር “ታሊባን ያውቅ ነበር”


የአልቃይዳውን መሪ አይማን አል-ዛዋሂሪ
የአልቃይዳውን መሪ አይማን አል-ዛዋሂሪ

የአልቃይዳውን መሪ አይማን አል-ዛዋሂሪን ስለመግደላቸው እርግጠኞች መሆናቸውን የዋይት ኃውስ ከፍተኛ ባለሥልጣናት አስታወቁ።

የታሊባን ከፍተኛ መሪዎችም ግለሰቡ አፍጋኒስታን ውስጥ እንደነበር ያውቁ እንደነበር የተናገሩት ባለሥልጣናት ካቡል ውስጥ ባለፈው ሣምንት መጨረሻ በድሮን በተጣለው ጥቃት የተገደለው አል-ዛዋሂሪ ብቻ መሆኑን ገልፀዋል።

የባይደን አስተዳደር ለታሊባን የቅድሚያ መረጃ አለመስጠቱን፣ ጥቃቱ የተፈፀመው በሰው አልባ ጄት መሆኑን፣ የአሜሪካ ወታደሮች በሥፍራው እንዳልነበሩ ተናግረዋል። ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ትናንት፤ ሰኞ ባደረጉት ንግግር “አሜሪካ በሚሳዪል ባደረገችው ጥቃት በዓለም እጅግ ተፈላጊ ከነበሩት አሸባሪዎች አንዱን ገድላለች” ብለዋል።

ባለፉት አሥርት ዓመታት አል-ቃይዳን ሲመራ የቆየው አይማን አል-ዛዋሂሪ መስከረም 1/1994 ዓ.ም. አሜሪካ ላይ ከተፈፀመው የሽብር ጥቃት ወዲህ ቡድኑ መርቡን በዓለም ላይ ሲዘረጋ መቆየቱ ተነግሯል።

ግድያውን ያወገዙት የታሊባን ቃል አቀባይ ዙቢሁላ ሙጃሂድ “ድርጊቱ በታሊባን እና በሌላ ወገን በተሰለፉት በአሜሪካና በምዕራብ ሃገሮች መሪዎች መካከል ካታር ዋና ከተማ ዶሃ ላይ ከሁለት ዓመታት በፊት የተደረገውን ሥምምነት የሚጥስ ነው” ብለዋል።

አይማን አል-ዛዋሂሪ ያለበትን ለጠቆመ 25 ሚሊዮን ዶላር ወሮታ ለመክፈል አሜሪካ ቀደም ሲል ማስታወቂያ አውጥታ ነበር።

XS
SM
MD
LG