በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአሜሪካው ነፃነት በአብዮት ጦርነት


የዩናይትድ ስቴትስ ባንዲራና የመንግሥቱ ዓርማ የሆነው ንስር አሞራ
የዩናይትድ ስቴትስ ባንዲራና የመንግሥቱ ዓርማ የሆነው ንስር አሞራ

ዩናይትድ ስቴትስ 239ኛውን የነፃነት ቀኗን ሰኔ 27/2007 ዓ.ም ታከብራለች፡፡

በአብዮቱ ጦርነት ውስጥ የዛሬ 238 ዓመት የተሣተፈችው የፈረንሣይ የጦር መርከብ ሌርሚዮን ቀጥተኛ አምሣያ
በአብዮቱ ጦርነት ውስጥ የዛሬ 238 ዓመት የተሣተፈችው የፈረንሣይ የጦር መርከብ ሌርሚዮን ቀጥተኛ አምሣያ

please wait

No media source currently available

0:00 0:07:47 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ዩናይትድ ስቴትስ 239ኛውን የነፃነት ቀኗን ነገ፤ ሰኔ 27/2007 ዓ.ም ታከብራለች፡፡

የነፃነቱን አዋጅ የነደፉት ቤንጃሚን ፍራንክሊን፣ ጃን አዳምስ፣ ታመስ ጄፈርሰን፣ ራጀር ሼርማን እና ራበርት ሊቪንግስተን ነበሩ፡፡

የማሳቹሴትስ የጋራ ብልፅግና ገዥና የሁለተኛው አሕጉራዊ ጉባዔ ፕሬዚዳንት የነበሩት ጃን ሃንኩክ በአዋጁ ላይ ሰኔ 27/1968 ዓ.ም ፊርማቸውን አኖሩ፡፡ ከአንድ ወር በኋላ ሐምሌ 26/1768 ዓ.ም የታላቋ ብሪታንያ ቅኝ የነበሩት ሌሎቹ ግዛቶችም ሰነዱን ተቀላቀሉ፤ ነፃነታቸውንም አወጁ፡፡

በአብዮቱ አራማጆች አሜሪካዊያን እና በእንግሊዝ ጦር መካከል ከ1767 ዓ.ም እስከ 1775 ዓ.ም ድረስ ለስምንት ዓመታት የዘለቀ ጦርነት ተካሂዷል፡፡

ሰሞኑን የ18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ትውስታ ተመልሶ መጥቷል፡፡ ፈረንሣዊያን ያኔ አሜሪካዊያን ከእንግሊዝ ቅኝ ነፃ ለመውጣት ያደርጉ በነበረው ውጊያ አግዘዋቸዋል፡፡

በጦርነቱ ላይ ተሣትፋ የነበረችው ሌርሚዮን የምትባለው የጦር መርከብ አምሣያ ተሠርታ ሰሞኑን ኒው ዮርክ ገብታለች፡፡

ለተጨማሪ ዝርዝር የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG