በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ የ2020 የህዝብ ቆጠራ


ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በመጪው ዓመት የህዝብ ቆጠራ በሚካሄድበት ወቅት በሀገሪቱ የሚኖሩት ሰዎችን ሁሉ ዜግነት መጠየቅን ያካትት እንደሆነ ዛሬ በከፍተኛ ፍ/ቤት ክርክር ተደርጎበታል።

በየአሥርተ ዓመቱ በሚካሄደው የህዝብ ቆጣራ የዜግነት ጥያቄ ሲነሳ ለብዙዎቹ መልሱ ከባድ አይሆንም። እዚህ ለተወለዱ አሜሪካውያን ወይም ወደዚህ አገር ከመጡ በኋላ ዜግነቱን ለተቀበሉት መልሱ የአሜሪካ ዜጋ ነኝ ነው።

ነገር ግን ህገወጥ ፍልሰትን በመቃወም ረገድ ጠንካራ አቋም ያላቸውና ከሜክሲኮ ጋር በሚያዋስነው የአሜሪካ ድንበር ላይ ግንብ ለመግንባት የሚፈልጉት ፕሬዚዳንት ትረምፕ በሀገሪቱ ያሉት ህጋዊ ሰነድ የሌላቸው ፍልሰተኞች ብዛት እንዲታወቅ ሲሉ በህዝብ ቆጠራው ወቅት የዜግነት ጥያቄ እንዲነሳ ይፍልጋሉ። እአአ ከ1950 አንስቶ እንዲህ አይነት ጥያቄ ሲቀርብ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG