No media source currently available
ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ ምክንያት ሊደርስ የሚችለውን የሰብል ጉዳት ለመከላከል የደረሱ ሰብሎችን በአስቸኳይ መሰብሰብ እንደሚያስፈልግ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ። ወቅቱን ያልጠበቀው ዝናብ ‘አሳስቦኛል’ ያለው የደቡብ ወሎ ግብርና መምሪያም ተማሪዎች የመንግሥት ሠራተኞችና የፀጥታ ኃይሉ በሰብል ስብሰባው ላይ ተሣትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አስተላልፏል።