በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሚያንማር የጸጥት ሃይሎች የሮሂንጋ ሙስሊሞች ሰብአዊ መብት መርገጡን ቀጥለዋል

አንድ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለስልጣን እንደሚሉት የሚያንማር የጸጥት ሃይሎች በሰሜን ምዕራብ ራኺን ክፍለ-ግዛት የቀሩትን ሮሂንጋ ሙስሊሞች ሰብአዊ መብት መርገጡን ቀጥለዋል።

አንድ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለስልጣን እንደሚሉት የሚያንማር የጸጥት ሃይሎች በሰሜን ምዕራብ ራኺን ክፍለ-ግዛት የቀሩትን ሮሂንጋ ሙስሊሞች ሰብአዊ መብት መርገጡን ቀጥለዋል።

ሚያንማር ውስጥ በሮሂንጋዎች ላይ የሚፈጸመው የዘር ማጽዳት ተግባር እየቀጠለ ነው ይላሉ በተባበሩት መርንግስታት ድርጅች የሰብአዊ መብት ጉዳይ ዋና ጸሀፊ አንድሪው ጊልሞር።ጊልሞር ዛሬ ባወጡት መግለጫ ይህና ያሉት በቅርቡ በጎረቤት ሀገር ባንግላደሸ በተፋፈጉ የሰደተኛ ሰፈሮች ከተጠለሉ ሮሂንጋዎች ባገኙት ምመረጃ መሰረት ነው።

ወደ 700,000 የሚጠጉ ሮሂንጋዎች የሚንያማ የጸጥታ ሀይሎች ከሚያደርሱባቸው ስቃይ በመሸሽ ካለፈው ነሃሴ ወር አንስቶ ባንግላደሽ ገብተዋል። የሮሂንጋ እማኞችና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እንደሚሉት የሀገሪቱ ወታደራዊ ሃይል በሮሂንጋዎች ላይ ግድያ አስገድዶ መድፈርና በእሳት የማጋየት ተግባር ይፈጽማል

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG